Get Mystery Box with random crypto!

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማጣራት እንዲደረግባቸው በተለያዩ ተቋማት ከቀረቡለት የትምህርት ማስረጃዎች | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማጣራት እንዲደረግባቸው በተለያዩ ተቋማት ከቀረቡለት የትምህርት ማስረጃዎች ውስጥ እስካሁን 21 ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ማግኘቱን አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ ተቋማት የግለሰቦች የትምህርት ማስረጃ ተገቢነት ተጣርቶ እና ተረጋግጦ እንዲገለጽ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት በ42 የትምህርት ማስረጃዎች ላይ በሁለት ዙር ባካሄደው የህጋዊነት ማረጋገጫ ሥራ 21ዱ ሐሰተኛ ሆነው መገኘታቸውን የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር አሳውቋል።

ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃው በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ስም ተጭበርብሮ በተሰራ ማሕተም፣ በአመራር የስምና የማዕረግ ቲተር እንዲሁም በሐሰተኛ ፊርማ ተመሳስሎ የተሠራ መሆኑ ተመላክቷል።

ግለሰቦቹ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በመጠቀም በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በመምህርነት ተቀጥረው በመስራት የማይገባቸውን ጥቅም እያገኙ መሆኑም ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው የሐሰተኛ ትምህርት አጣሪ ግብረ ኃይል አቋቁሞ ሰፊ የማጣራት ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy