Get Mystery Box with random crypto!

በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የስራ ፈጠራ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተጀመረ፡፡ በአርቲፊሻል ኢን | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የስራ ፈጠራ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተጀመረ፡፡


በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የተዘጋጀው ይህ ስልጠና የአስር ቀናት ቆይታ ይኖረዋል፡፡ ስልጠናው በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የስራ ፈጠራ ላይ ትኩረት አድርጓል፡፡
ስልጠናው በዘርፉ የተሰማሩ ወጣቶችን በማነቃቃት በስራ ፈጠራው ዘርፍ የሚታዩ ተግዳሮቶችን ከመቅረፍ ባሻገር መሠረታዊ የእውቀት እና ክህሎት ክፍተቶችንም እንደሚሞላ ይጠበቃል፡፡
ስልጠናውን በይፋ ያስጀመሩት  ከኢንስቲትዩቱ ምርምር እና ልማት ዘርፍ የተወከሉት አቶ የኋላእሸት መገርሳ ናቸው፡፡ ስልጠናው በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የስራ ፈጠራ ዙሪያ የሚታየውን የግንዛቤ ክፍተት በመሙላት ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው አቶ የኋላእሸት ጠቁመዋል፡፡
በተለይም በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ስታርት አፕ (ጀማሪ ተቋማትን) የተመለከቱ የሰው ኃይል ልማት ስራዎች በስፋት አለመኖራቸውን የገለጹት ተወካዩ ኢንስቲትዩቱ ያዘጋጀው ይህ እድል መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ መልካም አጋጣሚ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ሰላሳ ሁለት ተሳታፊዎችን በመያዝ የተጀመረው መርሓ ግብር፤ ሰልጣኞች በዘርፉ የሚኖራቸውን የስራ ፈጠራ ሀሳቦች ወደተግባር እንዲቀይሩ የሚያስችል እድልም መመቻቸቱ  ከመድረኩ ተመላክቷል፡፡
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy