Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል ከ1 ሺሕ 200 በላይ ትምህርት ቤቶች መደበኛ ትምህርት መጀመራቸው ተገለጸ በትግራ | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

በትግራይ ክልል ከ1 ሺሕ 200 በላይ ትምህርት ቤቶች መደበኛ ትምህርት መጀመራቸው ተገለጸ

በትግራይ ክልል ከሚያዝያ 23 ጀምሮ በ1 ሺሕ 218 ትምህርት ቤቶች መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት መጀመራቸው ተገለጸ።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ኪሮስ ጉዑሽ (ዶ/ር) እንደገለጹት በክልሉ ከሚገኙ 1 ሺሕ 466 ትምህርት ቤቶች መካከል 1 ሺሕ 218 ትምህርት ቤቶች ላይ ከሚያዚያ 23 ጀምሮ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት ተጀምሯል፡፡

ትምህርት በመጀመሩ በተማሪዎችና አስተማሪዎች መካከል ናፍቆትና የትምህርት ጥማት መስተዋሉን ገልጸው ይህም በትምህርቱ ማኅበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረ ጠቁመዋል፡፡
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy