Get Mystery Box with random crypto!

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በ2015 የመውጫ ፈተና ለሚፈተኑ ተመራቂ ተ | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በ2015 የመውጫ ፈተና ለሚፈተኑ ተመራቂ ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በበይነ መረብ/online የታገዘ ሞዴል የሙከራ ፈተና መሰጠቱን የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ሰለሞን ጉንታ ገልጸዋል።

የሙከራ ፈተናው ተማሪዎችን ለአገረ-አቀፍ የመውጫ ፈተና በሚያግዛቸው መልኩ የተዘጋጀ መሆኑን ያመላከቱት ዲኑ፤ ፈተናው ከተመረጡ ትምህርት ዓይነቶች (Core Competence) መውጣቱ ተማሪዎችን ለፈተናው በተገቢው ያዘጋጃቸዋል ብለዋል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በበይነ መረብ በመታገዝ የተሰጠውን ሞዴል ሙከራ ፈተና በኮሌጁ ዘጠኝ የትምህርት ክፍሎች በቅድመ ምረቃ መደበኛ የትምህርት መርሃ ግብር በ2015 ዓ.ም የሚመራቂ 182 ተማሪዎች መፈተናቸውን ዶ/ር ሰለሞን ተናግረዋል።

በቀጣይ ለኮሌጁ የተከታታይ ትምህርት መርሃ ግብር ቅድመ ምረቃ ተመራቂ ተማሪዎች በበይነ መረብ በመታገዝ ሞዴል የሙከራ ምዘና የሚሰጥ መሆኑን በመጠቆም።

የኮሌጁን ተማሪዎች ለመውጫ ፈተና ዝግጁ እንዲሆኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወኑን የገለጹት የኮሌጁ ዲን፤ በቀጣይ ጊዜ ተፈታኝ ተማሪዎችን የበለጠ ለማዘጋጀት በትጋት እንሰራለን ብለዋል።

በመጪው ሀምሌ ወር በሀገር አቀፍ ደረጃ በኦንላይን የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና 310 ያህል የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ኮሌጅ ተማሪዎች ፈተናውን የሚወስዱ መሆኑን ነው ዶ/ር ሰለሞን ያሳወቁት።

በኮሌጁ ፈተናውን ከሚወስዱ አጠቃላይ ተፈታኞች መካከል 182 የመደበኛ እንዲሁም 128 የተከታታይ ትምህርት መርሃ ግብር ተማሪዎች ሲሆኑ፤ በጾታ ስብጥር 256 ወንድ እንዲሁም 54ቱ ሴቶች ናቸው። #WSU
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy