Get Mystery Box with random crypto!

በፈተናው ስዓት ማድረግ ያሉብን ጥንቃቄዎች 1.መቅረጫ ይዞ ገብቶ የእርሳሱ ጫፉ ሲሰበ | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

በፈተናው ስዓት ማድረግ ያሉብን ጥንቃቄዎች
1.መቅረጫ ይዞ ገብቶ የእርሳሱ ጫፉ ሲሰበር ወይም ሲያልቅ ከመቅረፅ ይልቅ በዛ ያሉ የተቀረፁ እርሳሶችን ይዞ መግባት ተገቢ ነው።ሌላኛው ደግሞ ይዘናቸው የምንገባቸው የእርሳስ እና የላጲስ በመልስ መስጫው ወረቀት በምንሳሳትበት ጊዜ እርሳሱም ሆነ ላጲሱ ቶሎ ሚለቅ ማያጎላ ማለትም ከቀባን ብሀላ ልቀቅ አተልቀቅ ብለን መታገል የለብንም በቅድመ ዝግጅት መለየት እና ተዘጋጅቶ መጠበቅ ይገባናል።
2.በፈተናው በምንሰራበት ወቅት የተሰጠንን ስዓት በአግባቡ መጠቀም ይኖርብናል።1እና2 ከባድ ጥያቄዎች ብለን ብዙ ቀላል ጥያቄዎችን ማጣት የለብንም።ስለሆነም የተሰጠንን ስዓት በአግባቡ መጠቀማችን ውጤታችን ይወስነዋል።ለማንለውጠው ነገር መጨነቅ የለብንም።ከተጠራጠርንም ቢሆን ከፈተናው ወረቀት አክብበን በመሄድ ስዓት እና ጊዜ ሲኖረን ተመልሰን በመሄድ መስራት ይኖርብናል።በፍፁም ግን መስራት የለለብን ስህተት በሀላ ተመልሰንን እንሰራዋለን ብሎ ዘሎ ማለፉ ዋጋ ስለሚያስከፉል በትኩረት መታየት ይገባዋል።እንደተባለው ከሆነ ፈታኞቹ የuniversity መምህራን ከሆኑ ጋሸ አንድ ጥያቄ ሁለት በማርያም በፈጣሪ ብሎ ከመለማመጥ ይልቅ በተሰጠን ሰዓት አጠናቀን መገኘት ይገባናል ቤተሰብ።ልንለውጠው በማንችለው ነገር ላይ ጊዜአችንን ማጥፍት፣መጨናነቅ የለብንም ምክንያቱም
ልንለውጠው ስለማንችል በሌላ በኩል ደግሞ ልንለውጠው በምንችለው ነገር ላይ መጨነቅ መጠበብ ፈፅሞ አይገባንም ምክንያቱም ልንለውጠው ስለምንችል በርቱልኝ ቤተሰብ ከጎናቹህ ነኝ።
3.ቤተሰብ ሌላው ደግሞ መርሳት የለለብን ነገር የአዕምሮ ዝግጅት ሊኖረን ይገባል።የግድ ብዙ ማንበብ መጨናነቅ አይጠበቅብንም በትንሽ ስዓት ብዙ ምዕራፍ መሸፈን እንዴት እንደምንችል ማወቅ ሌላኛውም ደግሞ ብዙ ጥያቄዎች በማስተዋል ምንመልሳቸው ሞልተዋል።እኛ የሚጠበቅብን የአምዕሮ ዝግጁነት ነው።ማለትም ከአሁኑ ጀምራቹህ እሰራዋለሁ ከኔ አዕምሮ በላይ አይሆንም ሁሉንም ጥያቄ እመልሰዋለው የሚል ዝግጅት ሊኖረን ይገባል ቤተሰብ።

Join our main channel

@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
JOIN FOR MORE

https://t.me/Grade12StudentsPreparation