Get Mystery Box with random crypto!

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች “ ስልጡን አገልጋይነት ለሁለንተናዊ ስኬታማነት “በሚል ርዕስ በተዘ | Ministry of Education Ethiopia

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች “ ስልጡን አገልጋይነት ለሁለንተናዊ ስኬታማነት “በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ውይይት አደረጉ፡፡
...................................................

የካቲት 1/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) "ከእዳ ወደምንዳ" በሚል ሀገራዊ መልዕክት እንደ ሀገር በተዘጋጁ የውይይት ሰነዶች ላይ ለትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ለሁለት ቀናት የተሰጠው ስልጠናና ውይይት ተጠናቋል፡፡

“ ስልጡን አገልጋይነት ለሁለንተናዊ ስኬታማነት “በሚል ርዕስ በቀረበው ሰነድ የሪፎርሙ መዋቅር ከተቋማት ባህሪና ተልእኮ አንጻር የተቃኘ መሆኑ ፣ ብቃትን ማዕከል ያደረገ፣ ነጻ ፣ ገለልተኛና አካታች ሲቪል ሰርቪስ መገንባት፣ ግልጽና የማትጊያ ሂደቶችንም የተከተለ ስርዓት ማበጀትን ዓላማው ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በመሆኑም በትምህርቱ ዘርፍ ለሚተገበሩ የሪፎርም ስራዎች ስኬታማነት በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና ሰራተኞች ለውጤታማነቱ የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ በከፍተኛ አመራሩ ተገልጿል ፡፡

በመድረኩ ላይ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ አስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ ( ዶ/ር ) “ ስልጡን አገልጋይነት ለሁለንተናዊ ስኬታማነት “በሚል ርዕስ ሲቪል ሰርቪስን የተመለከተ የመወያያ ሰነድ አቅርበዋል፡፡

በቀረበው ሰነድ መነሻ በትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ የአጠቃለይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት አየለች እሸቴና የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ኮራ ጡሹኔ መሪነት ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ዝርዝሩ

https://www.facebook.com/share/p/hyLBGNab4wnKpsoS/?mibextid=9R9pXO