Get Mystery Box with random crypto!

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች በሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እካሄዱ፡፡ == | Ministry of Education Ethiopia

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች በሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እካሄዱ፡፡
====================
ጥር 30/2016(ትምህርት ሚኒስቴር) ከ”እዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ መልዕክት እንደ ሀገር በተዘጋጀው የውይይት ሰነድ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡

የውይይቱ አላማ ሰራተኛው በሀገራዊና ክልላዊ የፖለቲካ፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የሰላም ሁኔታ ላይ በመወያየትና በመመካከር የተሻለ ግንዛቤ በመፍጠር መሆኑ ተገልጿል።

ውይይቱ በመጀመርያ ቀን ውሎው ሀብት የመፍጠር ጉዟችን፣ እያጋጠሙን ያሉ ተግዳሮቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች በሚል ርእስ የተዘጋጀ የውይይት መነሻ ሰነድ በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራአስፈፃሚ ኤባ ሚጅና(ፒኤችዲ) ቀርቧል።

በቀረበው ሰነድ መነሻ በትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ የአጠቃለይ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት አየለች እሸቴና በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ኮራ ጡሹኔ መሪነት ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ውይይቱ ዛሬም አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልፅግና በሚል ርእስ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴርን መረጃዎች በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ