Get Mystery Box with random crypto!

#ማስታወቂያ በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ በ20 | Ministry of Education Ethiopia

#ማስታወቂያ

በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ በ2016 በጀት አመት የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን አቅም ለማጎልበት የሚያግዝ ልዩ የስልጠና መረሃግብር ለማዘጋጀት እየሰራ ይገኛል።

በዚሁ መሰረት ስልጠናው የመምህራንን የስልጠና ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ እንዲሆን ለማድረግ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ከሚገኙ መምህራን መርጃ ለመሰብስብ የሚያስችል የበይነ መረብ መጠይቅ ተዘጋጅቷል።

በመሆኑም በማንኛውም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሒሳብ፣ እንግሊዘኛና የተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዓይነቶችን የምታስተምሩ መምህራን
https://forms.office.com/r/B8GAUYUg4H

ላይ በመግባት የተዘጋጀውን መጠይቅ እንድትሞሉና ለሚዘጋጀው ስልጠና ጥራት አስተዋፅኦ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የትምህርት ሚኒስቴር!