Get Mystery Box with random crypto!

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአደንዛዥ እጽና መድሃኒቶች ሥርጭት ለመከላከል በትኩረት መሰራት እንዳ | Ministry of Education Ethiopia

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአደንዛዥ እጽና መድሃኒቶች ሥርጭት ለመከላከል በትኩረት መሰራት እንዳለበት ተገለፀ።
----------------- //--------------------
ጥር 26/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) በአደዛዥ እጽና መድሃኒቶች ሥርጭት ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የአስተዳደር ጉዳዮች ዴስክ ኃላፊ አቶ አብዶ ናስር በዩኒቨርሲቲዎች የአደንዛዥ እጽና መድሃኒቶች ተጠቃሚነት ችግሮችን ለመከላከል ሥራዎች ሲሰሩ የቆዩ ቢሆኑም ከችግሩ ስፋትና ባህሪ አንጻር የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት እንዳልተቻለ ገልጸዋል፡፡

አቶ አብዱናስር አክለውም ችግሩን ለመፍታትም አደንዛዥ እጾችና መድሃኒቶች ወደ ተቋማቱ እንዳይገቡ ከባለድርሻ አካላት ጋር የቁጥጥር ስራዎችን ከመስራት ጎን ለጎን በጉዳዩ አሳሳቢነት ዙሪያ መንስኤዎችን፣ልምዶችንና መፍትሄዎችን መሠረት ያደረጉ የባህሪ ለውጥ ሊያመጡ በሚችሉ የተማሪ ሥልጠናዎች ላይ ማተኮር እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጤንነቱ የተጠበቀ ትውልድ ለመቅረፅ ፤ ስብዕናን በመገንባትና ግንዛቤ በመፍጠር የባህሪ ለውጥ ለማምጣት በትኩረት መሰረት እንደሚገባም ገልጸዋል።

ሀላፊው አክለውም ጉዳዩ የሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት በችግሩ አሳሳቢነት ልክ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በቅንጅትና በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሙሉ ዜናው

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0qG8vx8mBtALovuwLTZfPpvKo8BoYHqjmH92H9sLYGDN6JnYwLev3nr6YofkgzwxTl&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO