Get Mystery Box with random crypto!

#የቀን ለውጥ ማስታወቂያ ረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት ለመስጠት ሀሙስ የተጠራው ስብሰባ ወደ | Ministry of Education Ethiopia

#የቀን ለውጥ ማስታወቂያ

ረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት ለመስጠት ሀሙስ የተጠራው ስብሰባ ወደ አርብ የካቲት 1/2016 ዓ.ም ጠዋት 3:30 ሰዓት መሸጋገሩን ስለማሳወቅ

የትምህርት ሚኒስቴር: -

1. የአጠቃላይ ትምህርት የመምህራን የደረጃ እድገት የአፈጻጸም መመሪያ፣
2. የር/መምህራን፣ የም/ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የምልመላ መረጣና ምደባ የአፈጻጸም መመሪያ፣
3. የቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ዕጩ መምህራን ምልመላና መረጣ የአፈጻጸም መመሪያ፣ የሚሉ 3 መመሪያዎችን አዘጋጅቷል።

መመሪያዎቹ በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት አስተያየት ሰጥተውባቸው የዳበሩ ሲሆን የፌደራል አስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ክፍል 2 ንዑስ ክፍል 2 አንቀጽ 10 መሰረት የሚዘጋጁ መመሪያዎች ከመጽደቃቸው በፊት ማንኛውም ሰው የሚሳተፍበት የውይይት መድረክ ማዘጋጀትና ግብዓት መሰብሰብ እንዳለበት ስለሚደነግግ ሚኒስቴሩ የውይይት መድረከ አዘጋጀቷል።

በዚህም መሰረት አርብ የካቲት 01/2016 ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ለባለድርሻ አካላት የገለጻና የውይይት መድረክ ስለተዘጋጀ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ በመገኘት አስተያየት እንድትሰጡ ተጋብዛችኋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ