Get Mystery Box with random crypto!

ምርምሮች ሀገራዊ የትኩረት መስኮችን ያማከሉና ችግር ፈቺ ሊሆኑ ይገባል' ዶ/ር ሰለሞን ቢኖር | Ministry of Education Ethiopia

ምርምሮች ሀገራዊ የትኩረት መስኮችን ያማከሉና ችግር ፈቺ ሊሆኑ ይገባል" ዶ/ር ሰለሞን ቢኖር (የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ)
...................................................
ታህሳስ 13/2016 ዓ/ም (ትምህርት ሚኒስቴር) የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንቶች ፎረም ተጠናቀቀ።

በትምህርት ሚኒስቴር የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሰለሞን ቢኖር በፎረሙ ማጠቃለያ ምርምር ለሀገር እድገትና ልማት ያላቸውን አስተዋጾ ጠቅሰው ፎረሙ ሀገራዊ የምርምር ስራ ማነቆዎችን በመለየት በሳይንሳዊ መንገድ ግንዛቤ መፍጠር ይጠበቅበታል ብለዋል።

ዶ/ ሰለሞን ምርምሮች ሀገራዊ የትኩረት መስኮችን ያማከሉና ችግር ፈቺ ሊሆኑ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ከአፈጻጸም አንጻርም የከፍተኛ ትምህርት ፣ ቴክኒክና ሞያ ሥልጠና፣ ምርምር ተቋማትና ኢንዱሰትሪ ትስስር አዋጅ 1298/2015 ጋር እያጣጣሙ መተግበር እንደሚገባ አመላክተዋል።

የማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎች እውቀት መር መሆን እንዳለበት የጠቀሱት መሪ ስራ አስፈጻሚው መምህራን በእውቀታቸው ማህበረሰቡን በሚያገለግሉበትና ማህበረሰቡ ጋ ያሉ ሀገር በቀል እውቀቶችንም በሚጠቀሙበት አግባብ ሊመራ እንደሚገባው ገልጸዋል።

ሙሉ ዜናው

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0HPx5wyvSEJViDxPotEobRe2NJTh48j2fVDrTgoFCZBePzLUwg4rEgx8xcm2pRRASl&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO