Get Mystery Box with random crypto!

በትምህርት ስርዓቱ ላይ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት ትኩረት ሰጥቶ መረባረብ እንደሚገባ ተገለፀ። … | Ministry of Education Ethiopia

በትምህርት ስርዓቱ ላይ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት ትኩረት ሰጥቶ መረባረብ እንደሚገባ ተገለፀ።
…………………………………………………………………………………………………
ታህሳስ 17/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) በትምህርት ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ኤጁኬሽን ዴቨሎፕመንት ትረስት (EDT) ሲሰራቸው የነበሩ ስራዎችን ማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉቀን ንጋቱ ባለፉት አራት ዓመታት Education Development Trust (EDT) በርካታ ስራዎችን ሲሰራ እንደነበር አንስተዋል።

በተለይም የትምህርት ቤት አመራር ስልጠና እንዲሁም የትምህርት መረጃ ስርዓትን ማሻሻል ላይ የሠራቸው ስራዎች አሁን በትምህርት ሚኒስቴር ቁልፍ ጉዳዮች ተደርገው ተለይተዋል ብለዋል።

በዚህም የማስተማርና የትምህርት ቤት አካባቢ የየተሟላ እውቀትና ልምድ ያላቸው የትምህርት ቤት አመራሮችን ለመፍጠር በትኩረት እየተሠራ ይገኛልም ብለዋል።

ዛሬ በትምህርት ስርዓቱ ላይ ትኩረት ሰጥተን ካልተረባረብን ነገ የሚፈለገውን ለውጥ ማምጣት አንችልም ያሉት ስራ አስፈፃሚው ያለውን ሀብት በአግባቡ በመጠቀም በትምህርት ዘርፍ ለውጥ ማምጣት ይገባልም ነው ያሉት።

ሙሉ ዜናው
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid021HYrNui4s41fbzsNK3Ds5SNPq3zt5RRPnxQRDR6hBfbmAC5YAgo8mVJHrwJkjZXol&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO