Get Mystery Box with random crypto!

የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኚት ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንቶች ፎረም በቦንጋ ከተማ ተጀመረ ...... | Ministry of Education Ethiopia

የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኚት ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንቶች ፎረም በቦንጋ ከተማ ተጀመረ
.............................................
ታህሳስ 12/2016 ዓ/ም (ትምህርት ሚኒስቴር) የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኚት ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንቶች ፎረም በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተጀመሯል።

በፎረሙ ማስጀመሪያ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ እንደሀገር የሚሰሩ ምርምሮች ችግር ፈቺ ፣የምርምር ስነምግባር የተከተሉና የምርምር መስፈርቶች ያሟሉ ሊሆኑ እንደሚገባ ገልጸዋል ።

በምርምርና ማህበረሰብ ጉድኚት ዘርፍ ዩኒቨርስቲዎች የተሻለ ውጤታማ ለመሆን እርስ በርስና ከአለም አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ትብብር መመስረትና ማጠናከር እንደሚገባም ተናግረዋል ።

የቦንጋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጰጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ቦንጋ ዩኒቨርስቲ በምርምርና ማህበረሰብ ጉድኚት ዘርፍ ዉጤታማ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኚት ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሰለሞን ቢኖር ፎረሙ በሁለት ቀን ውሎው በከፍተኛ ትምህርት ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ምርምር ተቋማት እና ኢንዱስትሪ ትስስር አዋጅ ቁጥር 1298/2015 ፣ በከፍተኛ ትምህርት ምርምርና ማህበረሰብ ጉድኚት ማስፈጸሚያ መምሪያዎች፣ እንዲሁም የተመረጡ ዩኒቨርስቲዎች የምርምር ተግባራት አፈጻጸም ላይ ይመክራል ብለዋል።

ሙሉ ዜናው

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0WEsXBugxxedNmFW7rV4vwqkqV4nEpysY8vH3B9MKVgzywKNxhKfArKp1eS1xX9dPl&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO