Get Mystery Box with random crypto!

የሩሲያ መንግስት በትምህርት መስክ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ። | Ministry of Education Ethiopia

የሩሲያ መንግስት በትምህርት መስክ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ታህሳስ 10/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) የኢፊዲሪ ትምህር ሚኒስትር ክቡር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ከሩሲያ ፌዴሬሽን ትምህርት ሚኒስትር እና ከሌሎች የሩሲያ የትምህርትና ምርምር ተቋማት የተውጣጡ ልኡካንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ሚንስትሩ ከልኡካኑ ጋር በነበራቸው ቆይታ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ ፌዴሬሽን መካከል ያለውን የቆየ የትምህርትና ሥልጠና ትብብር እንዲሁም አሁን ላይ በሀገራችን ተግባራዊ እየሆነ ያለውን የትምህርት ስርአት ፣መዋቅር እና ሰትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች አስመልከቶ ገለጻ አድርገዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ያለውን ርብርብ የገለጹ ሲሆን በማያያዝም በመጪዎቹ አመታት የትምህርት ዘርፉን ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ እየተከናወኑ ያሉ ሰፋፊ የሪፎርም ስራዎችን አብራርተዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሸኔ በበኩላቸው የሩሲያ መንግስት በትምህርቱ ዘርፍ ለኢትዮጵያ እያደረገ ስላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በማያያዝም የሩሲያ መንግስት የሚያደርገው ድጋፍ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እና የሰው ሀብት ልማትን ለማሳደግ ሚናው የጎላ በመሆኑ ትብብሩን በቀጣይ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ከፍተኛ ፍላጎት ያለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሙሉ ዜናው

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02acg4VDWqNxxqz47thaDxGhKgrT2KxK3iyJN3Kh2k49XPUNhQvcfHabBew9M59mc2l&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO