Get Mystery Box with random crypto!

የኢፊዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከጣሊያን አቻው ጋር የትብብር መግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡ : | Ministry of Education Ethiopia

የኢፊዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከጣሊያን አቻው ጋር የትብብር መግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
ታህሳስ 2/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር እና የጣሊያን የትምህርት ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና መስክ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የትብብር መግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

በሁለቱ ወገኖች የተፈረመው የትብብር ስምምነት ሰነድ በሀገራቱ መካከል የሚደረገውን የትምህርትና ስልጠና ትብብር ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ስምምነቱን የኢፌዲሪ ትምህርት ሚንስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የጣሊያኑ አቻቸው ክቡር ጉሴፔ ቫልዳይታራ የፈረሙ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት መካከል ስትራቴጂክ የሆነ የትምህርትና ሥልጠና ትብብር እንዲኖር ያስችላል ተብሏል፡፡

የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በፊርማ ስነ ስረዓቱ ላይ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየተከናወኑ ያሉ የሪፎርም ስራዎችን ያብራሩ ሲሆን በተለይም ለሁሉም ዜጋ ያለምንም የኢኮኖሚ ደረጃ ልዩነት ፍትሃዊና ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ለማቅረብ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አብራርተዋል፡፡

የጣሊያኑ የትምህርት ሚኒስትር ክቡር ጉሴፔ ቫልዳይታራ በበኩላቸው ሀገራቸው በቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና፣በቋንቋና ባህል እንዲሁም በተማሪዎችና መምህራን ልውውጥ ላይ ከኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በትብብር ለመስራት ፍላጎት ያላት መሆኑን ገልፀገልፀል።


ሙሉ ዜናው ttps://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02ShLCdD4eRN8pEP3zqh8ryQ5bSJpHzWE3q3uv5Mk4tGtysWn3gCJfDKmSoewf3GCal&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO