Get Mystery Box with random crypto!

'በትብብርና አለም አቀፍ ተሳትፎ የሀገራችንን የአካዳሚክ ጉዳዮች ማስተዋወቅ ይገባል' ዶ/ር ሀብታ | Ministry of Education Ethiopia

"በትብብርና አለም አቀፍ ተሳትፎ የሀገራችንን የአካዳሚክ ጉዳዮች ማስተዋወቅ ይገባል" ዶ/ር ሀብታሙ አበበ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት
.............................................

ህዳር 28/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) የከፍተኛ ትምህርት የኮሙዩኒኬሽንና አለም አቀፍ ግንኙነት አመራሮች በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የኮሙኒኬተሮች ፎረም እያካሄዱ ነው።

በፎረሙ ላይ የተገኙት የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሀብታሙ አበበ ይህ መድረክ በትምህርት ዘርፉ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ላይ ልምድ ለመለዋወጥ ያግዛል ብለዋል።

በተለይም በአለም አቀፍ የአካዳሚክ ምህዳር ላይ የትብብር ድልድይ ለመገንባት የህዝብ ግንኙነትና አለም አቀፍ ክፍሎች ሚና የጎላ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም ሀገራችንን በአካዳሚክ ጉዳዮች በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ የተጠናከረ ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ መሥራት እንደሚጠበቅም ተናግረዋል።

በተጨማሪም ይህ መድረክ ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን ተሞክሮና አዳዲስ ስልቶች ላይ እርስ በርስ ልምድ ለመለዋወጥ እንዲሁም የትምህርት ሚኒስቴርን የሪፎርም አጀንዳዎች በሚገባ በመረዳት ለማህበረሰቡ የምናስተዋውቅበትን እድል ይፈጥራልም ብለዋል።

ሙሉ ዜናው

።https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0gQpNhitnjifce9LQgK76YR4wocLdrzV5XQTAguMzUG7WCCZeJs9RrJ3QwDFHLVZKl&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO