Get Mystery Box with random crypto!

ማስታወቂያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን በእንግሊዝኛ ቋንቋ መማራቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ (Letter | Ministry of Education Ethiopia

ማስታወቂያ

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን በእንግሊዝኛ ቋንቋ መማራቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ (Letter of proficiency) እንዲጻፍላቸው ለሚፈልጉ ተገልጋዮች ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ሲመጡ ማሟላት የሚጠበቅባቸው መሥፈርቶች: -
1. አሥራ ሁለተኛ ክፍል ማጠናቀቃቸውን የሚገልጽ ኦሪጅናል ሰርተፊኬትና የማይመለስ አንድ ኮፒ፣
2. በቀድሞው የትምህርት ፖሊሲ 10ኛ ክፍል አጠናቀው የመሰናዶ ትምህርት (ፕሪፓራቶሪ) ያላጠናቀቁ ከሆነ 10ኛ ክፍል ማጠናቀቃቸውን የሚገልጽ ኦሪጅናል ሰርተፊኬትና የማይመለስ አንድ ኮፒ፣
3. አመልካቾች ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ከማይመለስ አንድ ኮፒ ጋር ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን አገልግሎቱ የሚሰጥባቸው ቀናት ሰኞ እና ሐሙስ በሥራ ሰዓት መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር