Get Mystery Box with random crypto!

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች 18ኛውን የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን አከበሩ ………… | Ministry of Education Ethiopia

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች 18ኛውን የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን አከበሩ
……………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………….

ህዳር 26/2016 ዓ/ም (ትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች 18ኛውን የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን አከበሩ።

በትምህርት ሚኒስቴር የሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ተፈራ በበዓሉ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን የኢትዮጵያዊነት ሚዛንን በጠበቀና የአንድነታችንን ገመድ ባጠናከረ ሁኔታ ሊከበር ይገባል ብለዋል።

የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች መብትና እኩልነታቸው ህገ መንግስታዊ እውቅና እና ጥበቃ ያገኘበት ታሪካዊ ዕለት መሆኑን ጠቅሰው ራስን ማስተዳደር መብትን ጨምሮ ባህልና ቋንቋቸው በማሳደግ ሰፊ ርቀት መጓዝ መቻላቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።

“ብዝሀነትና እኩልነት ለአገራዊ አንድነት “ በሚል መሪ ቃል በተከበረው በዓል ላይ በትምህርት ሚኒስቴር የማህበራዊ ሳይንስ ስርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ አቶ ዑመር ሰይድ በህገ መንግስትና በህብረብሄራዊ ፌዴራሊዝም ላይ ያተኮረ የመወያያ ሰነድ አቅርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et
ይከታተሉ