Get Mystery Box with random crypto!

የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) እና ’HUWAWEI’ ለ | Ministry of Education Ethiopia

የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) እና ’HUWAWEI’ ለትምህርት ሚኒስቴር የ ICT መሳሪያዎች ድጋፍ አደረጉ
----------------------------//-------------------------
ታህሳስ 4/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) ዩኔስኮ-ሁዋዌ ቴክኖሎጂ ለአይሲቲ መሠረተ ልማት ማጎልበቻ የሚሆን ከ16 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ለትምህርት ሚኒስቴር አስረክቧል፡፡

በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ የአይሲቲ መሳሪያ ልገሳው ተማሪዎች ለትምህርታቸው ግብዓት ለማግኘት፣ እውቀታቸውን ከመማሪያ መጽሀፍት በላይ ለማስፋት እና ሰፊ ከሆነው አለም አቀፍ የመረጃ እና የመማር ልምድ ጋር እንዲገናኙ ያስችላቸዋል ብለዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለውም ተማሪዎች መሳሪያዎቹን በሃላፊነት በመጠቀም በቴክኖሎጂ ታግዘው ችግር ፈቺዎች እና የነገ መሪዎች እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ትምህርት ላይ ማተኮር እንደሚገባቸውም ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታዋ እንደ ሀገር ካለው የተማሪ ቁጥርና የትምህርት ቤቶች ብዛት አንጻር ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

ሙሉ ዜናው

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0278e5bCHaBR87kqfBmpvRtmX6ekBXyPBD94XHepZMmS2mPzU3SbkjdUwWTub8mvByl&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO