Get Mystery Box with random crypto!

የኤርትራ መንግስት በቀይባህር ጉዳይ ከማንም ጋር ለድርድር እንደማይቀመጥ አሳወቀ የኤርትራ መረጃ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

የኤርትራ መንግስት በቀይባህር ጉዳይ ከማንም ጋር ለድርድር እንደማይቀመጥ አሳወቀ

የኤርትራ መረጃ ሚኒስቴር ባወጣዉ አጭር መግለጫ በቀይባህር ጉዳይ ከማንም ጋር ለድርድር እንደማይቀመጥ አሳዉቋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስለ ውሀዊ አካሎችና ስለ ባህር በሮች የተባለውንና ''ተብሏል'' የተባለው ነገር ቁጥር የለውም ያለዉ ሚኒስቴሩ በዚም ያልተገረመ ታዛቢ የለም ሲል ገልጿል።

የኤርትራ መንግስትም እንደሁልጊዜው በእንደዚህ ዓይነቱ ጉዳዮች ላይ ለውይይት እንደማይታደም ማረጋገጡን ዳጉ ጆርናል ከሚኒስቴሩ ያገኘዉ መረጃ ያመላክታል።

ይህ ነገር ይመለከተናል የሚሉ ሁሉም አካላት ጉዳዩን እንዳይነኩት የኤርትራ መንግስት አስጠንቅቋል። በቅርቡ በመንግስት የመገናኛ ብዙኃን በተሰራጨ መልዕክት ጠ/ሚ ዐቢይ የባህር በር ጉዳይን አንስተዉ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ማወያየታቸዉ ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news