Get Mystery Box with random crypto!

በቤኒሻንጉል ክልል የኢቦላ ቫይረስ እንዳይከሰት ስጋት መኖሩ ተነገረ በደቡብ ሱዳን እና በሱዳን የ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

በቤኒሻንጉል ክልል የኢቦላ ቫይረስ እንዳይከሰት ስጋት መኖሩ ተነገረ

በደቡብ ሱዳን እና በሱዳን የኢቦላ ቫይረስ ተጠርጣሪዎች መገኘት እና ሞት መመዝገቡን ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ ይገባል የሚል ስጋት እንዳለ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቃል።

በተለይ በሱዳን የተፈጠረውን የእርስ በእርስ ግጭት ተከትሎ የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ወደ ክልሉ በአጎራባች ወረዳዎች በኩል በከፈተኛ  ሁኔታ ከመግባታቸው ጋር ተያይዞ በሽታው ሊገባ እንደሚችል ተገልጿል።

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ጤና ቢሮ የህብተሰብ ጤና ጣቢዎች ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ፍቃዱ አየለ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በሱዳን ዳባላይ በምትባል ስፍራ ከ150 በላይ በበሽታው የተጠረጠሩ ሰዎች እንዳሉ የተነገረ ሲሆን እሱን ለማጣራት ከዓለም የጤና ድርጅት እና ከሌሎች አካላት አካላት ጋር በመሆን ጥናት እየተደረገ ይገኛል።

በሽታው ቢያጋጥም ለይቶ ማቆያ የተዘጋጀ ሲሆን በሽታው በቀላሉ ሊገባ የሚችል በመሆኑም በባለሙያዎች  የተለያዩ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል።የበሽታው ምልክቶች  ከፍተኛ የሆነ ራስ ምታት፣ ትኩሳት፣ የጉሮሮ ፣ የሆድና የመገጣጠሚያ ህመም ፣ ድካም፣ የምግብ ፍለጎት መቀነስ እና በተለያዩ የሰውነት ቀዳዳዎች ደም መፍሰስ  ናቸው፡፡

በመሆኑም በሽታው ከታየበት ሀገር  የጉዞ ታሪክ ያለውና ምልክቶቹ ከታዩ በአቅራቢያ ወደ ሚገኘው የህክምና ተቋማት እንዲሄዱ ማድረግን ጨምሮ ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የመለየት ስራ በመስራት መረጃ በትክክል መያዝ እንዳለበት አቶ ፍቃዱ አየለ ተናግረዋል።

ከፌደራል ጤና ኢንስቲትዩት እና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የተለያዩ  ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አቶ ፍቃዱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news