Get Mystery Box with random crypto!

የፖሊስ ልብስ በለበሱ ሰዎች ታግቼ ነበር ያለው ሾፌር የጫነውን ንብረት መሸጡ ተደረሰበት!! የፀጥ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

የፖሊስ ልብስ በለበሱ ሰዎች ታግቼ ነበር ያለው ሾፌር የጫነውን ንብረት መሸጡ ተደረሰበት!!

የፀጥታ ኃይል ልብስ በለበሱ ሰዎች ታግቼ ከ2 ሚሊዮን ብር  በላይ ንብረት ተዘርፍኩ ያለው አሽከርካሪ ንብረቱን  ሸጦ የሀሰት ክስ መመስረቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

አሽከርካሪው ሰኔ 9 ቀን 2015 ዓ/ም የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-35747 ኢ/ት በሆነ ተሽከርካሪ አዳማ ከሚገኝ ድርጅት ግምቱ 2 ሚሊዬን 7መቶ ሰላሳ ሺ 240  ብር የሚያወጣ የፌሮ ብረት መርካቶ ከሚገኝ የግል ተበዳይ ሱቅ ለማራገፍ ይጭናል።

የፀጥታ ኃይል ልብስ የለበሱ አካላት ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ አግተው ንበረቱን እንደዘረፉት በአቃቂ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለቃሊቲ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ያመለክታል፡፡

ፖሊስ ጣቢያው ለጉዳዩ ልዮ ትኩረት በመስጠት ወንጀል ፈፃሚዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ንብረቱን ለማስመለስ ባደረገው በርቱ ክትትልና ባሰባሰበው መረጃ አሽከርካሪው ብረቱን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ  ወረዳ 13 አካባቢ ሸጦ ተሽከርካሪውን ጀሞ አካባቢ ማቆሙን ይደርስበታል፡፡

በግለሰቡ ላይ ምርመራው ቀጥሎ ከተሰረቀው ንብረት መካከል ግምቱ 648ሺ 432 ብር የሚያወጣ ብረት ማስመለሱን ፖሊስ ጣቢያው አስታውቋል። የተጣለበትን እምነት ወደኋላ በማለት ንብረቱን ሸጦ ሳይታገት ታግቻለሁ በማለት ፖሊስን ለማሳሳት ሀሰተኛ ክስ የመሰረተው አሽከርካሪ እና  የተሰረቀውን ንብረት የገዛውን ጨምሮ በአጠቃላይ  ሁለት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን መቀጠሉን ፖሊስ አስታውቋል።

አንዳንድ ግለሰቦች ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በማቀድ ሳይታገቱ ታግተናል በማለት ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጬ እና ሳይዘረፋ ተዘርፈናል በማለት የግል ጥቅማቸውን በህገወጥ መንገድ ለሟሟላት የሚሯሯጡ መኖራቸውን ያስታወቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ የተለያዩ ሚዲያዎች የእነዚህ ህገወጦች መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ መልእክቱን አስተላልፏል ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news