Get Mystery Box with random crypto!

#Update የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ የጋራ የፀጥታ ዕቅድ ላይ ምክክር መ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ የጋራ የፀጥታ ዕቅድ ላይ ምክክር መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።

በመድረኩ፦
- የትምህርት ሚኒስቴር፣
- የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች፣
- የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች፣  የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች እና የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ፤ ከሐምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በ102 የፈተና ጣቢያዎች የሚካሄደው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሀገራዊ የፀጥታ ሁኔታውንና የክረምቱን የአየር ሁኔታ ያገናዘበ በርካታ የሰው ኃይል መመደቡን አሳውቋል።

ፈተናው ከሥርቆት በፀዳ መልኩ እንዲካሄድ ሁሉም ኃላፊነቱን ወስዶ በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባም ኮሚሽኑ አሳስቧል።

በአማራና በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች በፈተና ጣቢያዎች የፀጥታ ችግሮች እንዳይከሰቱ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በቂ ዝግጅት ማድረጉንም ኮሚሽኑ አሳውቋል።

ተማሪዎች ለፈተና ሲመጡ ፦

- የሀኪም ማዘዣ የሌለው መድሃኒት በሽሮፕም ሆነ በታብሌት፣
- የህክምና መስጫ መርፌ፣
- የአንገት ሀብል፣
- የፀጉርና የጆሮ ጌጥ፣
- ከጋብቻ ቀለበት ውጭ ፈርጥ ያለው የጣት ቀለበት እና የእጅ አንባር አድርገው መምጣት እንደማይችሉ ፖሊስ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

በተጨማሪም ፦
- ተንቀሳቃሽ  ስልክ፣ 
- አይ-ፓድ፣
- ታብሌት፣
- ላፕቶፕ፣
- ስማርት ሰዓት፣
- ሲዲ፣
- ሚሞሪ ሪደርና ኦ-ቲጂ ኮንቨርተር እንዲሁም ፎቶ የሚያነሱ እና ድምፅ የሚቀርፁ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ይዞ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ተገልጿል።

የተከለከሉ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲዎቹ ግቢ ውስጥም ሆነ በዙሪያው ይዞ መገኘት፣ ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት እንዲሁም በዩኒቨርሲቲ ግቢ ወስጥ በግልም ሆነ በቡድን ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው።

ይህንን ተላልፎ በተገኘ ተማሪ ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ አንዳንድ የትራንስፖርት ችግሮችን ለመቅረፍ፣ ለተማሪዎች ከትምህርት ቤት ጀምሮ በወረዳና በዞን ትምህርት ቢሮ አማካኝነት የፈተና መመሪያ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት እንደተደረገ መሆኑን አሳውቋል።

መረጃው የፌዴራል ፖሊስ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news