Get Mystery Box with random crypto!

ሸዋሮቢት በሸዋሮቢት ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ የሸዋሮቢት ከተማ ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት | ኢትዮ መረጃ - NEWS

ሸዋሮቢት

በሸዋሮቢት ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ

የሸዋሮቢት ከተማ ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን አስታውቋል፡፡

ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ በሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር እና በአካባቢዋ የሚተገበሩ የክልከላ ውሳኔዎች ማስተላለፉን ዛሬ ባወጣው መግለጫው አስታውቋል።

በዚህም መሰረት፡-

1) መጠጥ ቤቶች እስከ ምሽት 4 ሰዓት

2) እግረኛ እስከ ምሽቱ 5 ሰዓት

3) ባጃጅና ሞተር ሳይክል እስከ ምሽት 1 ሠዓት ድረስ ብቻ መንቀሳቀስ የሚችሉ መሆኑን ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል።

የከተማዋ ኮማንድ ፖስት፤ በከተማዋ ይበልጥ ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር የተጣሉ ክልከላዎችን በማክበርና በማስከበር ኹሉም የኅብረተሰብ ክፍል በሀላፊነት በመንቀሳቀስ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ በመግለጫው አሳስቧል፡፡
 
@sheger_press
@sheger_press