Get Mystery Box with random crypto!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ2016 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት የበጀት አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ2016 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት የበጀት አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ!!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 21ኛ መደበኛ ስብሰባ የ2016 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ የበጀት አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የፌዴራል መንግስት የ2016 በጀት በአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ የተቀመጡ ግቦችን ታሳቢ በማድረግ፣ የሀገር ደህንነት ከማስጠበቅ፣ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጐችን ከመርዳት፣ በህግ ማስከበር ዘመቻው የወደሙ መሰረተ ልማቶች መልሶ ከማቋቋም፣ በቀጣይ ሊኖር የሚችለውን የማህበራዊና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎችና ዓላማዎች ከማሳካት አኳያ የተቃኘ ሲሆን የ2016- 2020 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚና የፊሲካል ማዕቀፍን መሠረት በማድረግ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው፡፡

በዚሁ መሰረትም ለፌደራል መንግስት መደበኛ ወጪዎች ብር 369.6 ቢሊየን፣ ለካፒታል ወጪዎች ብር 203.9 ቢሊየን፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ ብር 214.07 ቢሊየን፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ ብር 14 ቢሊየን በጠቅላላው ብር 801.65 ቢሊየን ሆኖ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው የፌዴራል መንግሥት የ2016 በጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news