Get Mystery Box with random crypto!

'የራያ አላማጣ ግጭት በፕሪቶሪያዉ ስምምነት ጠላቶች የተደረገ እንጂ፤ በህወሓት ወይንም በትግራይ እ | ETHIO-MEREJA®

"የራያ አላማጣ ግጭት በፕሪቶሪያዉ ስምምነት ጠላቶች የተደረገ እንጂ፤ በህወሓት ወይንም በትግራይ እና በአማራ አስተዳደሮች መካከል አይደለም" ጌታቸዉ ረዳ

"የሕወሓት ኃይሎች በራያ በኩል ቀጥተኛ በሆነ ጥቃት "ለአራተኛ ጊዜ" ወረራ ከፍቷል" አብን


"በደቡብ ትግራይና በሌሎች በኃይል የተያዙ የትግራይ ግዛቶች ባኹኑ ወቅት የተፈጠረው ክስተት፤ በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ወይም በሕወሃት ወይንም በትግራይ እና በአማራ ክልሎች መካከል የተፈጠረ ግጭት አይደለም" ሲሉ፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ተናገሩ።

ጌታቸው ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ በኤክስ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ "ክስተቱ ኹለቱ ወገኖች የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እያደረጉት ያለውን አወንታዊ ግንኙነት ለማደናቀፍ የፈለጉ የስምምነቱ ጠላት የሆኑ ኃይሎች የፈጠሩት ነው" ሲሉ ፅፈዋል።

ከሩቅም ከቅርብም የግጭት ማቆም ስምምነቱ ጸር የሆኑ ኃይሎች ጦር እየሰበቁ መሆኑን የጠቀሱት ጌታቸው፤ ብቸኛው አዋጭ መንገድ ግን ሰላም ነው ብለዋል። ኹለቱ ወገኖች ችግሮችን ለመፍታትና የሚስማሙባቸውን ጉዳዮች ለማጎልበት አዲስ አበባ ውስጥ ስብሰባ ላይ መሆናቸውንም ጌታቸው አመላክተዋል።

   - ETHIO-MEREJA -
   T.me/ethio_mereja