Get Mystery Box with random crypto!

ባለፉት ሶስት ቀናት ከሶስት ሺ በላይ ኢትዮጵያውያንን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል | ETHIO-MEREJA®

ባለፉት ሶስት ቀናት ከሶስት ሺ በላይ ኢትዮጵያውያንን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል ተባለ

ከሚያዚያ 04 እስከ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ለሶስት ቀናት በተከናወነ ዜጎችን #ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ ከሶስት ሺ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተገለጸ።

ትላንት ሚያዚያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም በሶስት ዙር በረራ በተከናወነ በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1 ሺህ 192 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በዕለቱ ወደ ሀገር ከተመለሱ 1 ሺህ 192 ዜጎች ውስጥ 1078 ወንዶች፣ 89 ሴቶች፣ 5 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እና 20 ጨቅላ ህፃናት መሆናቸውን ጠቁሟል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል ብሏል፡፡

   - ETHIO-MEREJA -
   T.me/ethio_mereja