Get Mystery Box with random crypto!

መንግስት በሳዑዲ አረብያ እስር ቤቶች የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ ጀመረ! | ETHIO-MEREJA®

መንግስት በሳዑዲ አረብያ እስር ቤቶች የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ ጀመረ!

በሳዑዲ አረብያ እስር ቤቶች እና ማቆያ ማዕከላት ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ውስጥ የመመለስ ስራ በይፋ መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

መንግስት በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ 70 ሺህ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው እንደሚመልስ መግለጹ ይታወሳል።ይህንን ተከትሎም ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ በይፋ የተጀመረ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት በሁለት በረራዎች 842 ኢትዮጵያዊያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ አገር ቤት መግባታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብዩ ተድላ እንደገለፁት መንግሰት በቀጣይ አራት ወራት በሳኡዲ አረቢያ በእስር ላይ የሚገኙ ከ70 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገር ቤት ለማስመለስ እቅድ ይዞ እየሰራ ነው።ስራውን ለማስጀመር 16 የመንግስት ተቋማትን በአባልነት ያቀፈ ብሄራዊ ኮሚቴ የተዋቀረ ሲሆን የማስመለስ ሂደቱን ለማስጀመር ኮሚቴው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ወደ ሳኡዲ በመጎዝ ከሃገሪቱ መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር የዝግጅት ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል።

በተያዘው እቅድ መሰረት ዜጎችን ለመመለስ በሳምንት 12 በረረዎችን በቀጣይ አራት ወራት በተከታታይ የሚደረግ መሆኑም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።በውጭ ጉጋይ በሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራ የመንግስት የልዑካን ቡድን ወደ ሳዑዲ አረቢያ በማቅናት ከጅዳ አስተዳደሮች ጋር ውይይት በማድረግ በእስር ቤትና ማቆያ ጣብያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን መጎብኘቱ ይታወሳል።

   - ETHIO-MEREJA -
   
T.me/ethio_mereja