Get Mystery Box with random crypto!

#ቦሌ የአዲስ አበባ ፖሊስ “የሽበር ጥቃት ለመፈፀም ተልዕኮ ይዘው ሲንቀሳቀሱ” ነበር ባላቸው “የ | ETHIO-MEREJA®

#ቦሌ

የአዲስ አበባ ፖሊስ “የሽበር ጥቃት ለመፈፀም ተልዕኮ ይዘው ሲንቀሳቀሱ” ነበር ባላቸው “የፋኖ አመራርና አባላት ላይ እርምጃ ወሰድኩ” አለ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ ሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ቀትር ላይ ባወጣው መግለጫ “በፅንፈኛው #የፋኖ አመራርና አባላት ላይ እርምጃ ተወሰድኩ” ሲል አስታውቋል።

“የፅንፈኛው አመራርና አንድ የቡድኑ አባል ሲገደሉ አንደኛው በቁጥጥር ስር ውሏል” ብላል።

ናሁሰናይ አንድአርጌ ታረቀኝ፣ አቤኔዜር ጋሻው አባተ እና ሀብታሙ አንድአርጌ ተሰማ የተባሉት “የፅንፈኛው ፋኖ ቡድን አባላት” በመዲናዋ የሽበር ጥቃት ለመፈፀም ተልዕኮ ይዘው እየተንቃሰቀሱ መሆኑን የፀጥታ አካላት ባደረጉ ክትትል ደርሰውበታል ሲል የፖሊስ መግለጫ አስታውቋል።

ሂደቱን አስመልክቶ የፖሊስ መግለጫ እንዳመላከተው ተጠርጣሪዎቹ እንቅስቃሴ እያደረጉ ባለበት ሁኔታ ሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ/ም ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ሚሊኒዬም አዳራሽ አካባቢ የፖሊስ አባላት እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፍቃደኛ አልሆኑም ብሏል።

በዚህም በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2C 14373 አ/አ አይነቷ ሱዙኪ ዲዛዬር መኪናን በመጠቀም ከፖሊስ አባላት ጋር ቶክስ በመክፈታቸው “ናሁሰናይ አንዳርጌ ታረቀኝ” ቆስሎ ወደ ህክምና ከተላከ በኋላ ሲሞት ሌላኛው “ሀብታሙ አንዳርጌ ተሰማ” የተባለው ደግሞ በተኩስ ልውውጡ መሃል መገደሉን ጠቁሟል።

“አቤኔዘር ጋሻው አባት” የተባለው የቡድኑ አባል ሳይቆስል በቁጥጥር ስር መዋሉን አዲስ አበባ ፖሊስ በመግለጫው አስታውቋል፡፡2 የፖሊስ አባላቱ ሳጅን አራርሳ ተሾመ እና ኮንስታብል ማቲያስ ጴጥሮስ መቁሰላቸውን የጠቆመው ፖሊስ “አቶ እንዳሻው ጌትነት” የተባሉ ግለሰብ በፅንፈኛው አባላት ተገድለዋል ብሏል።

   - ETHIO-MEREJA -
   
T.me/ethio_mereja