Get Mystery Box with random crypto!

በፖለቲከኛ በቴ ኡርጌሳ ግድያ የተጠረጠሩ 13ሰዎች ታሰሩ!   በኦሮሞ ነጻነት ግንባር የፖለቲካ ኦፊ | ETHIO-MEREJA®

በፖለቲከኛ በቴ ኡርጌሳ ግድያ የተጠረጠሩ 13ሰዎች ታሰሩ!
 
በኦሮሞ ነጻነት ግንባር የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ የተጠረጠሩ 13 ሰዎችን ፖሊስ ማሰሩ ተዘገበ ።

አቶ በቴ የተገደሉበት መቂ የሚገኝበት የምሥራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ በአቶ በቴ ግድያ የተጠረጠሩ 13 ሰዎችን ማሰሩን የኦሮምያ ብሮድካስቲንግ ኔት ዎርክ ትናንት ማምሻውን በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል። ስለ ተጠርጣሪዎቹ ማንነት የወጣ ዝርዝር መረጃ የለም።

አቶ በቴ ማክሰኞ ምሽት በመንግሥት ኃይሎች በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ አስከሬናቸው በትውልድ ከተማቸው መቂ ከተማ ውስጥ እሮብ ጠዋት መንገድ ዳር ተጥሎ መገኘቱን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ አስታውቋል። የ41 ዓመቱ አቶ በቴ በየካቲት ወር ከፈረንሳዊው ጋዜጠኛ አንትዋን ጋሊንዶ ጋር ከታሰሩ በኋላ ባለፈው ወር ነበር በዋስ ከእስር የተለቀቁት።

ሆኖም በዚህ ሳምንት ማክሰኞ ምሽት ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 150 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በትውልድ ከተማቸው በመቂ ካረፉበት ሆቴል በመንግሥት ኃይሎች ታስረው መወሰዳቸውን የኦነግ ቃል አቀባይ ለሚ ገመቹ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት AFP ተናግረዋል። አቶ በቴ በዚያኑ ወቅት በከተማዋ ወደሚገኝ ማቆያ ማዕከል መወሰዳቸውን ለሚ ገልጸዋል። የአቶ በቴ ስርዓተ ቀብር ትናንት በትውልድ ስፍራቸው በመቂ ተፈጽሟል።

   - ETHIO-MEREJA -
   
T.me/ethio_mereja