Get Mystery Box with random crypto!

ዳግም ተፈታኞችም ሆኑ መደበኛ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ትምህርታቸውን በክረምቱ እንዲማሩ ክልሉ እየሰ | ETHIO-MEREJA®

ዳግም ተፈታኞችም ሆኑ መደበኛ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ትምህርታቸውን በክረምቱ እንዲማሩ ክልሉ እየሰራ መሆኑን ገለጸ!!

በግጭት አካባቢዎች ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በተሰጠው የዳግም መፈተን ዕድል መሠረት ተማሪዎች ውጤት እንዲያስመዘግቡና የመማር ማስተማር ሂደቱ ክረምቱን እንዲቀጥል እየሠራ እንደሚገኝ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሕዝብ ግንኙነትና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ዳግም በተሰጠው የመፈተን እድል ተማሪዎቹ ክረምቱን እንዲጠቀሙበት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡ክልሉ ረጅም ጊዜን በጦርነት ውስጥ በማሳለፉ ተማሪዎች በመማር ማስተማሩ ዙሪያ የሚጠበቀውን ትምህርት አለማግኘታቸውንና ተረጋግተውም መፈተን አለመቻላቸውንም አስታውሰዋል፡፡

አካባቢው በወረራና በጦርነት ውስጥ በመቆየቱ የክልሉ ሕዝብ ዋና ትኩረቱን ራስን ማዳን ላይ አድርጓል፡፡ ተማሪዎችም የዚሁ አካል ነበሩ፡፡ ስለሆነም ከዚያ ትኩረት እንዲወጡ ከስነልቦና ሕክምና ባሻገር ትምህርቱን የሚሸፍኑበትና ተረጋግተው የሚያጠኑበትን እድል ማመቻቸት ግዴታ እንደሆነም ነው አቶ ጌታቸው የተናገሩት፡፡ለዳግም ተፈታኞች በመደበኛው የመማር ማስተማር ሥራው ብዙ እድሎች ቢሰጥም፤ በቂ ነው ተብሎ ስለማይታመን የክረምት ትምህርትም እንዲቀጥል መታሰቡን ገልጸዋል፡፡

ትግበራው በጥናት እንዳይዘናጉ በማገዝ የረሷቸውን ነገሮች እንዲያስታውሱ ለማድረግ ያግዛል፣ ያልሸፈኗቸው ቦታዎች ካሉም ለመሸፈንና ለፈተና ዝግጁ እንዲሆኑ ያስችላቸዋልም ብለዋል፡፡እንደርሳቸው ማብራሪያ፤ መደበኛ የትምህርት ሥርዓቱ ከሰኔ 30 በኋላ ትምህርት የሚያበቃ ቢሆንም ትምህርት እንዳይቋረጥ ይደረጋል፣ ሐምሌና ነሐሴን ተፈታኞቹ ሳይዘናጉ ትምህርታቸውን ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡(አሚኮ)
T.me/ethio_mereja