Get Mystery Box with random crypto!

#ታሪፍ ማሻሻያ! የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ከነገ ሰኔ 01 2014 ዓ.ም | ETHIO-MEREJA®

#ታሪፍ ማሻሻያ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ከነገ ሰኔ 01 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያ አድርጓል።

ቢሮው ዝቅተኛውን የታሪፍ ማሻሻያ 50 ሳንቲም ማድረጉን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ይርጋለም ብርሃኔ ተናግረዋል።

ዝቅተኛው ኪሎ ሜትር 2.5 ኪ.ሜ፣ ረጅሙ ደግሞ 30 ኪ.ሜ መሆኑን ያነሱት ምክትል ሀላፊው፣በዚህም

በሚኒባስ/ ኮድ 1 ና ኮድ 3/ 2.50 የነበረው አሁን 3 ብር እንዲሁም
30 ብር የነበረው ደግሞ 33.50 መሆኑን እንዲሁም

በሚዲ-ባስ/ሃይገር እና ቅጥቅጥ/ ደግሞ ከ1 እስከ 2 ብር ጭማሪ ተደርጓል ብለዋል።

አዲሱ የዋጋ ጭማሪ ከነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ጋር ብቻ የተያያዘ መሆኑን አንስተዋል።አሊያንስ አዉቶቡሶች ከሚዲባስ ጋር የተገናኙ በመሆናቸው ጭማሪው እንደሚመለከታቸው እና አንበሳ እና ሸገር አዉቶቡሶች ግን በመንግሥት ድጎማ ስር በመሆናቸው ማሻሻያ እንዳልተደረገባቸው ተገልጿል።(ሼር)
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja