Get Mystery Box with random crypto!

ግንባታው ተቋርጦ የነበረው የብሔራዊ ቴአትር ህንፃ በድጋሚ በአዲስ መልክ ተጀመረ የኢትዮጵያ ብሄ | ETHIO-MEREJA®

ግንባታው ተቋርጦ የነበረው የብሔራዊ ቴአትር ህንፃ በድጋሚ በአዲስ መልክ ተጀመረ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ቤትን ለማዘመን በሚል ቴአትር ቤቱ በሚገኝበት ስፍራ ዘመናዊ አዲስ ህንጻ ለመገንባት ታቅዶ ወደ ተግባር ቢገባም የግንባታ ስራውን ለማከናወን ውል ወስዶ የነበረው ተቋራጩ አፍሮ ጺዮን ኮንስትራክሽ አማካይነት ግንባታው ቢጀመርም ከአንድ አመት በፊት ባጋጠመው መጓተት ሊቋረጥ እንደቻለ ተነግሮ ነበር፡፡

በ3 ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል በሚል 1.5 ቢሊዮን ብር ተመድቦለት ሲሰራ የነበረው አፍሮ ጺዮን በድጋሜ ውሉን ማደስ እንደሚፈልግ ሃሳብ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም የቀረበለትን መስፈርት ሊቀበል ባለመቻሉ ጥያቄው ውድቅ መደረጉ ይታወሳል።

በአሁኑ ሰዓት ኦቢድ ኮንስትራክሽን የተሰኘው አዲስ ተቋራጭ የወጣውን ጨረታ በማሸነፍ ግንባታውን እንደጀመረ የፌደራል መንግስት ህንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተክለጻዲቅ ተክለአረጋይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ተቋራጩ ከእዚህ ቀደም በነበረው ዲዛይን መሰረት የተቋረጠውን የግንባታ ሂደት በማስቀጠል በሶስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ህንፃውን ገንብቶ ለማጠናቀቅ ውል ማሰሩን ሃላፊው ገልጸዋል፡፡አዲስ የሚገነባው ህንጻ ባለ 12 ወለል እና ከሰባት ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ ሲሆን ፣1.5 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደሚጠይቅ ብስራት ሬድዮ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

አዲሱ ህንጻ የቴአትር መስሪያ ቦታዎችን ቁጥር ከመጨመሩም ባለፈ የጊዜውን ዘመናዊነት የሚያሟላና ሙዚየም ጨምሮ የተለያዩ መገልገያዎችን የሚይዝ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡
T.me/ethio_mereja