Get Mystery Box with random crypto!

#የችሎት ውሎ ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ በአስር ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንድትለቀቅ አዘ | ETHIO-MEREJA®

#የችሎት ውሎ

ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ በአስር ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንድትለቀቅ አዘዘ!

“ሮሃ ሚዲያ” የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና ባለቤት መዓዛ መሐመድ በአስር ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንድትለቀቅ በፍርድ ቤት ተወሰነ።

የመዓዛን የዋስትና ጥያቄ ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 30 ቀን 2014 የፈቀደው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። መዓዛ ከጓደኛዋ መኖሪያ ቤት በፖሊስ የተያዘችው ከአስር ቀናት በፊት ግንቦት 20 ቀን 2014 ነበር።

#በሌላዜና

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ የ10 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ በፍርድ ቤት ተፈቀደላቸው።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝና ሰለሞን ሹምዬ እያንዳንዳቸው የ10 ሺ ብር ዋስትና በማስያዝ ከእስር እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ሰጠ።

ፍርድ ቤቱ ፤ ፖሊስ በጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ እና በመስከረም አበራ ላይ እያደረገው ለሚገኘው ምርመራ ተጨማሪ ስድስት ቀናት ፈቅዷል። የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ትዕዛዙን ያስተላለፈው ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 30 ነው።
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_mereja