Get Mystery Box with random crypto!

#ምትኬ #ደራሲ_HiLA ክፍል 18 ሴና ያለ እናቷ ትንሽ ጊዜ ብታስቸግርም ውስጧ ነገራት መሰለኝ | ኢትዮ-ልቦለድ & ❤️❤️📚

#ምትኬ
#ደራሲ_HiLA
ክፍል 18
ሴና ያለ እናቷ ትንሽ ጊዜ ብታስቸግርም ውስጧ ነገራት መሰለኝ ለመደችው አሁን ዝምተኛ ልጅ ሆናለች፡፡ እናቴን እምታግዛት ልጅም ተገኝታለች ሂወት እንደገና መስመሯን እየያዘች ነው ጥሩ እየሄደች ነው ብሩኬ ካሰብኩት በላይ የዋህና ቅን ሰው ነው በየጊዜው መጥፎ ማንነቱን እያስወገደ መልካምነትን ይላበሳል የሴን ስድስት ወር እና የኔ እና የሱን ስድስት ወር በጥሩ ሁኔታ አክብረነዋል ከልጃችን የልደት ቀን ጋር የፍቅር ቀናችን በመግጠሙ የተለየ ደስታ ነበረው፡፡
ዛሬ ብሩኬ ቆንጆ ሆኜ እንድመጣ ብቻችንን ጊዜ ማሳለፍ እንዳለብን ነግሮኛል እራት አብረን እንድንበላ እያሰበ ነው ከመቼውም በላይ አምሬና ተውቤ ለአለባበስ ምርጫዬ ቤቲዬ እና እማዬ እጃቸው አለበት ከቤቲ ጋር ብቻችንን ስንሆን የልቤን ጠየኳት
"ቤቲ እንደው ልቤ ፈርቷል?"
" ለምን ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ?"
" ምንም ግን ብሩክ እስከዛሬ እንደዚህ አይነት ፕሮግራም ይዞ አያቅም በዛ ላይ ቤቲ ስሞኝ እንኳን አያቅም አንገቴን ወይ ግንባሬን ካልሆነ በቀር ዛሬ ግን ለምን እንደሆነ እንጃ ልቤ ፈርቷል"
"ውይ የኔ እህት አትፍሪ መቼም የወደፊት ሚስቴ ያላትን ሴት ደፍሮ አያስገድም አንቺ ደግሞ ውሳኔሽን እንደማትለውጪ ንገሪው ምን አልባት አንቺ ዝም ብለሽ ይሆናል እኮ እሱ አላሰበው ይሆናል"
"እንዳፍሽ ያርግልኝ የራሱ አይደለሁ ስንጋባ ይደርስ የለ ብቻ ፈራሁ?"
"አይዞሽ የኔ ቆንጆ አምሮብሻል ደሞ ከአይን ያውጣሽ"
ተዘጋጅቼ እንደጨረስኩ ለብሩኬ ደወልኩ እየመጣ እንደሆነ ነገረኝ ከዛም ብዙም ሳይቆይ በር ተንኳኳ ቤቲ ከፈተች ብሩኬ ነበር
" ሰላም ለዚህ ቤት? ደና ዋላችሁ የብሌን እናት?" ብሎ ቤቲን ሰላም ብሎ ገባ እማዬም ከጓዳ መታ ጨበጠችው አምሮበታል የተለየ ግርማን አላብሶታል የለበሰው ውሀ ሰማያው ሸሚዝ ከግሬይ ጨርቅ ሱሪው ጋር የሆነ ሙሽራ አስመስሎታል ብሩኬ አለባበስ ዝነጣ ይችልበታል ቁመቱ ተክለሰውነቱ ምንም ቢለብስ እንዲያምርበት ይረዱታል ፀጉሩ በሚገባ ተስተካክሏል ሸሚዙን የተወሰነ ያህል ከፍቶታል ያንገት ሀብሉ ከመሀተቡ ጋር ተዳምሮ እዛ ሰፊ ደረቱ ላይ የተለየ ግርማን አላብሰውታል በእጁ ያሰረው ቅንጡ የእጅ ሰአት ከሸሚዙና ከእጁ ጋር ተስተካክሎ ተቀምጧል የተጫመተው የቆዳ ጫማ በአግባቡ ተወልውሎ መሬት ላይ ለመራመድ ያሳሳል በአጠቃላይ ሳየው ልቤ ደግሞ ደነገጠለት ሌላ ሴት ባታየው ብዬ ተመኘሁ ሰውሬ ላስቀምጠው ፈለኩ
"የኔ እናት በጣም አምሮብሻል" የብሩኬ ንግግር ከሀሳቤ አባነነኝ
"እኔ ምለው ሳትነግሩን ልትጋቡ ነው? ወይስ ሰርግ አለባቹሁ?" ቤቲ ነበረች ጠያቂዋ "እውነቷን ነው ይሄ ሁሉ መሽቀርቀር ምንድነው?" እማዬም ቀጠለች "መቼም የብሌን እናት ወግና ስርአቱን ረስተን ይቺን ተጠብቃ የቆየች ውድ እንቁ ልጅ እንደ ፌስታል አከንጠልጥዬ አልወስዳት የናቷን ምርቃት ሳልቀበል ቤቴ ይዣት አልገባም ግን ዛሬ አብረን እንድናሳልፍ ነበር ፍላጎቴ ፈቃዶት ከሆነ"
"አብረን እንድናሳልፍ ስትል እንዴት ማለት ነው አልገባኝም" "ማለቴ ምሽቱን ከኔጋር እንድታሳልፍ ማለቴ ነው ቨሌላ ነገር አይውሰዱብኝ ብሌን ከነ ክብሯ መሆኗን አቃለሁ እኔም ከሰርጋችን በፊት ላልነካት በእግዚአብሔር ስም ቃል ለራሴ ገብቻለሁ ግን በቃ ዛሬ የተለየች ቀኔ ትሆን ዘንድ ፈለኩ መቼም ከሰርጋችን በፊት አልነካትም ፈጣሪ ምስክሬ ነው ግን ዛሬን አብራኝ እንድትሆን ይፍቀዱልኝ" ይሄን ሲያወራ ቤቲ እና እኔ እየተያየን ነው ደግሞ እንደማፈር እላለሁ እማዬ ፊቷ ላይ ምንም ማንበብ አቃተኝ ዝም ብላ ሁላችንንም ካስተዋለች በኋላ
"ይኸውልህ ልጄ ንቀከኝ ነው ብዬ አልልም ብትደፍረኝ ፍቃዴን አጠይቅም ግን እሳት እና ጭድ ጎን ለጎን ካሉ አንዱ አንዱን ያሸንፋል ያንን ነው ምፈራው በርግጥ ህፃናት አይደላችሁም ግን ከነ ክብሯ ነው ለባሏ መስጠት ያለብኝ ብዬ ስለማስብ ነው እንደው ፈጣሪ ባይፈቅድና አንተን ባታገባ ልጄ ሁለት ያጣች ትሆንብኛለች ወንድ ልጅ ደግሞ አንዴ ክብር እንደሌላት ካወቀ ካገኘችው ጋር እምትጋደም ነው አርጎ ሚስላት አልጋ ላይ ሊያቃት ሚገባው ባልዋ ብቻ ነው ስለዚህ አሁን አልከለክላችሁም ግን አደራ ብሌን እራስሽን ተቆጣጠሪ ሂዱ በሉ መልካም ጊዜ" ብሩኬ ከወገቡ ጎንበስ ብሎ እጇን ሳመ አመስግኖ ተያይዘን ወጣን ምንም ሳንነጋገር አንድ ሆቴል ጋር ስንደርስ መኪናውን አቆመ ብሩኬ ለምን እንደሆነ ባላቅም ያለ ወትሮው ዝምታው እጅግ በዛብኝ እኔም ውስጤ እጅግ ፈራ ለምን እንደሆነ ባላቅም መመለስ አማረኝ
ክፍል 19