Get Mystery Box with random crypto!

#ምትኬ #ደራሲ_HiLA ክፍል 17 ሴናን ከተኛችበት ብድግ አርጌ ማባበል ጀመርኩ እናቴ ትን | ኢትዮ-ልቦለድ & ❤️❤️📚

#ምትኬ

#ደራሲ_HiLA

ክፍል 17

ሴናን ከተኛችበት ብድግ አርጌ ማባበል ጀመርኩ እናቴ ትንሽዬ ብጫቂ ወረቀት ከሴና ስር አገኘች
" ልጄን አደራ ብሌን ልጅሽ ናት አልመለስም ከዚህ በኋላ " ይላል ወረቀቱ ገና ጡት ያልጠገበች ህፃን ጥላ መሄዷ እጅግ አበሳጨኝ ራስወዳድ ሆና ታየችኝ ይቺን ትንሽ ልዕልት ለመተው ከሆነ ለምን ወለደቻት እናትነት ክብሩን አጣብኝ ነገ ሴና አድጋ ማንነቷን ታሪኳን ስጠይቅ ምን ይመለስላታል ብቻ ግራ እየተጋባሁ ነበር
ሴናን እንደምንም አባብዬ እናቴን ጠየኳት
"እማ እንደው አንጀቷ እንዴት ቻለላት የወለደቻትን ለመጣል ቆይ ግን እናቴ እዚሁ ብትኖር ምን ትሆናለች"
"አይ የኔ ልጅ አንጀቷማ እንዴት ይችላል ብለሽ ማን ያውቃል ይህን ስትወስን ከራስዋ ጋር ስንቴ እንደተጣላች ምን አልባትም በሂወቷ ትልቁን ውሳኔ ይሆናል እያነባች የወሰነችው ወይ ደግሞ እንዳልሽው እራስ ወዳድ ሳትሆን የልጇን ነገ መስመር እያስያዘች እንዳለችውም ታሪክ እየፃፈችላት ይሆናል ብቻ አንድ ነገር እርግጠኛ እንደነበረች አስባለሁ ልጇን ቤተሰብ ሰታታለች እናት አርጋሻለች ለሷ ካንቺ የተሻለ እናት እንደማታገኝላት ታውቅ ነበር ከብሩክ የተሻለ አባትም ከየትም አይመጣም ስለዚ አሁን ልጄ ሰናይትን መውቀስ አቁሚ የሷን ጉዳት ማንም አይጎዳም ልጅሽን ብቻ አምነሽ ተንከባከቢ ነገ የሚሆነው አይታወቅም ፍርዱን ለባለቤቱ ስጪ"
በቃ እማ እንዲ ነች ማንንም አትወቅስም ማንም ላይ እጅ አጠቁምም ሁሉም ነገር የራሱ ምክንያት አለው ብላ ታምናለች መሆን ስላለበት ሆነ ትላለች፡፡ እማዬ የተለየች ናት ሁሌም እኔ በሆነ ጉዳይ በንዴት ስብሰለሰል የሆነ ነገር ብላ እንዳስብ ታረጋለች ከራሴ ጋር ታስታርቀኛለች፡፡ ዛሬም እንደ ሁልጊዜው አረጋጋችኝ ወደስራ መግባት ስለነበረብኝ ተነስቼ ሻወር ወሰድኩ ስጨነቅ ስናደድ ሻወር ያረጋጋኛል ቀጥዬ ለብሩኬ ደውዬ የተፈጠረውን ነገርኩት
" የኔ እናት በቃ አንቺ ተረጋጊ ሴናን እናሳድጋታለን ከስራ ስትወጪ በደንብ እናወራለን መቼም ልጃችን አትከብደንማ"
"አዎ ብሩኬ በቃ ላሳውቅህ ብዬ ነው ቻው እወድሃለሁ "
"እኔም የኔ እናት አፈቅርሻለሁ መልካም ቀን"
በዚሁ ጨራርሼ ስራ ገባሁ እማዬ እየገረመችኝ እየተደነኩ የስዋ ልጅ በመሆኔ እየተደሰትኩ ስራዬን መስራት ቀጠልኩ የሻይ ሰአት ላይ ከቤቲ ጋር አወራንበት ቤቲ በሚገርም ሁኔታ መጀመሪያውኑ ጠርጥራ እንደነበር ነገረችኝ ገረመኝ ብቻ ብዙ ነገር አወራን ቤቲዬ በሚገርም መንገድ እንዳየው አረገችኝ
"ብሌንዬ ምንአልባትም እኮ እናተጋር መኖሯ ለሷ ምቾት አልሰጣት ይሆናል አሁን እንደምታይው ኑሮው ከብዶ የለ ምንአልባት ስራ ለመስራት አስባ ይሆናል ጥላት የሄደችው ደግሞ ለእናቷ ነው የሰጠቻት አንቺ እኮ ክርስትና እናት ነው በሀይማኖታችን መቼም ክርስትና እናት ከእናት በላይ ነው መሆን ያለበት የቃልኪዳን ልጅሽ ናት ስለዚህ አልጣለቻትም ቤቷ እናቷ ጋር ጥላት ነው የሄደችው መቼም ትንሽ እሚከብደው አመት እንኳ ጡት ሳጠባ መሆኑ ነው እንጂ ብዙ አታካብጂው"
ልክ ናት እኔ የሴና እናት ነኝ ስለዚህ ሀላፊነት አለብኝ ሰናይት ግን የት ይሆን የሄደችው ስለሷ አንድ እንኳ እሚያቅ የለም ሰፈሯን እንጂ ቤት የላትም እስቲ ከብሩኬ ጋር ተነጋግረን እንወስናለን፡፡ ከስራ ስወጣ ብሩኬ መጥቶ ወሰደኝ አንድ ካፌ ቁጭ ብለን ማውራት ጀመረን
" ብሩኬ መጀመርያ እንዴት ብስጭት ብዬ እንደነበር እማዬና ቤቲ ሲያወሩኝ ተረጋጋሁ እንጂ"
" በቃ ተያት አሁን ስለ ልጃችን እናውራ ምን ተሻለ እማማ መቼም ብቻቸውን አይችሉም አይደል ?" ብሩኬ እናቴን እማማ ነው ሚላት እሷ ፊት ሲሆን ደግሞ የብሌን እናት ይላታል፡፡
" አዎ ግን እኮ ብሩኬ አሁን ላይ ባለው ሁኔታ ሞግዚት መቅጠር አልችልም የእማዬን ደስታ ፈልጋለሁ ቤት ላሳድስ ብር እያጠራቀምኩ ነው "
" አልገባኝም ቤቱን ለማሳደስ ሳነግሪኝ ነበር መደበቅ ጀመርሽ"
"ብሩኬ እንደዛ አይደለም ብዙ ነገር ተደራረበ ለዛ ነው ብነግርህ ካላሳደስኩ ትላለህ ወጪ በዛብሀ"
"እሺ ጥሩ አሁን ስለሱ አናወራም ሴናን እማማ ይንከባከቧ ቤት ውስጥ እምታግዛቸው ነገ እንፈልጋለን"
" እሺ ከየት እናገኛለን ጥሩ ሰው"
" ከደላላ ቤት ወይም በሰው በሰው እንፈልጋለን ሴናዬም እያደገች ነው 6 ወር ሊሆናት እኮ ነው አይገርምም"
"እኔ እና አንተም 6 ወር ሊሆነን ነው "
"አዎ አንቺ ፍቅሬን ከተቀበልሽ እኔ ካፈቀርኩሽ ግን ከዛ በላይ ሆኖኛል ብሌን መቼ ነው ሚስቴ ማረግሽ" አንዳች ነገር ውስጤን ወረረው እንባዬም መጣ ደስም አለኝ
"ፈጣሪ ሲፈቅድ ነዋ ባሌ ምትሆነው"
"ብሌኔ ከኔበፊት ፍቅረኛ ይዘሽ ታቂያለሽ? ወንድስ ታውቂያለሽ?"
"አንተ ስንት ሴት ታውቃለህ? የኔን ከመመለሴ በፊት "
"በፍቅር ከሆነ አንድ ሴት ናት ልቤንም ማንነቴንም የቀማኝችን ሙሉ ያረገችኝ በስሜት ከሆነ ግን ብዙ ሴት አውቃለሁ የአንድ ለሊት ትውውቅ ሲነጋ መልኳን እማላስታውሳት ብዙ ሴት አውቃለሁ ብሌን በፍቅር የመጀመሪያዬም የመጨረሻዬም ነሽ"
"እኔ ግን ካንተ ውጪ ማንንም አላቅም ለፍቅርም ለሁሉም የመጀመሪያዬ ነህ የመጨረሻዬ እንድትሆን ምኞቴ ነው "
ብዙ ነገር አውርተን ፍቅር ተነጋግረን የተወሰነ እቅዶች አውጥተን ወደ ቤት ሸኘኝ ሴናንም በዛው አይቷት ወጣ.....

ክፍል 18