Get Mystery Box with random crypto!

#ምትኬ #ደራሲ_HiLa ክፍል 4 ጨርሼ ቡኩን ስመልስ በእጁ የያዘውን የመቶ ብሮች ኖት እየሰጠ | ኢትዮ-ልቦለድ & ❤️❤️📚

#ምትኬ
#ደራሲ_HiLa
ክፍል 4
ጨርሼ ቡኩን ስመልስ በእጁ የያዘውን የመቶ ብሮች ኖት እየሰጠኝ
"ጉርሻ ነው ያዢው አለኝ " በሂወቴ እንደዛ ተበሳጭቼ አላቅም ባንክ ቤት ውስጥ ያሉት በሙሉ በሁኔታዬ ተገርመው ዞሩ፡፡ ጭራሽ ስራ ቦታ መሆኔን ረሳሁት ብሩን ፊቱ ላይ በትኜ በስድብ አጥረገረኩት
"ትሰማለህ እኔ ብሌን ያንተን ልቅም ቃሚ ገንዘብ አልፈልግም የፈለከውን ነገር ጨርሰሀል መሰለኝ እባክህ ካጠገቤ ሂድ ሌላ ውርደት እንዳትከናነብ"
ቤቲ መታ ጎትታ ይዛኝ ወጣች ከዛም
"ያምሻል እንዴ ልጁ እኮ ልማዱ ነው ደግሞ የባንኩ ደንበኛ ነው ባለሀብትም ጭምር?"
"አያገባኝም ቤቲ ትሰሚያለሽ እኔ ክብሬ ይበልጥብኛል የሱ ሀብት ለኔ ምኔም አይደለም"
"ብሌንዬ ልክ ነሽ ለነገሩ ደግ አረግሽ ልጁ ለሴት ክብር የለውም ከሰው ይለቅ ገንዘቡን ያከብራል ደግ አረግሽ"
በዚመሀል ማናጀሩ አስጠራኝ
"ተረጋጊ እሺ እሱ ፊት አትርበትበቺ"
ወደ ማኔጀሩ ቢሮ ገባሁ
"ብሌን ዛሬ የተፈጠረውን ማስረዳት ትችያለሽ ደንበኛን ማክበር ነበረብሽ እስቲ ልስማሽ ቀጥይ"
ከእልህና እምባ ጋር አቀላቅዬ የተፈጠረውን ሁሉ ነገርኩት
"እሺ በቃ ለሌላ ጊዜ ትዕግስተኛ ሁኚ በስራ አለም ብዙ ነገር ያጋጥማል አሁን ተረጋጊ እና በቃ ወደቤት ሂጂ "
"በጣም አመሰግናለሁ ስራውን መስራት ግን ችላለሁ"
"ካልሽ እሺ" እንደምንም ራሴን አረጋግቼ ወደ ስራ ተመለስኩ ጨርሼ ወደ ቤት ስወጣ ቤቲ ቀጠሮ አለኝ ብላ ተለየችኝ ብቻዬን በእግር መጓዝ ስጀምር ከኋላዬ መኪና ይከተለኛልመጀመሪያ ላይ ብዙም አላስተዋልኩትምየዛሬ ውሎዬን እያሰብኩ የልጁ ንቀት እያበሳጨኝ ነበር እቤት ገብቼ ለእናቴ እስክነግራት ቸኩያለሁ በመሀል ዞር ስል ግን መኪናው በጣም በዝግታ ሲከተለኝ አስተዋልኩ እንደመቆም ብዬ ላሳልፈው ስል መኪናውም ቆመ አሁን በጣም ማሰብ ጀመርኩ በግሬ ወክ ማረግ ብፈልግም ልቤ እየፈራ ስለነበር ከሩጫ ባልተናነሰ አካሄድ ነበር የምጓዘው ወደ ሰፈሬ የሚወስደውን ቅያስ ስታጠፍ ጭር ብሎ ነበር መኪናውም ከኋላዬ መከተሉን አላቆመም ነበር፡፡ ትንሽ እንደተጓዝኩ ቀድሞኝ ከፊቴ መንገዴን ዘጋብኝ ......

ክፍል 5 ይቀጥላል ከተመቻችሁ
#join #share