Get Mystery Box with random crypto!

#ምትኬ #ደራሲ_HiLa ክፍል 3 እናቴን እያሰብኩ ፈገግታዬን መግታት አቃተኝ የስራ ሰአቴን ጨ | ኢትዮ-ልቦለድ & ❤️❤️📚

#ምትኬ
#ደራሲ_HiLa
ክፍል 3
እናቴን እያሰብኩ ፈገግታዬን መግታት አቃተኝ የስራ ሰአቴን ጨርሼ ወደቤት ስመለስ ለናቴ የሙሉ ቀን ውሎዬን ዘከዘኩላት ተሳስቀን መርቃኝ ብር ላይ መጠንቀቅ እንዳለብኝም መከረችኝ፡፡
ስራ ከጀመርኩ ቀን ቀንን እየተካ ሳምንትን አርግዞ ወርን ወለደ፡፡ ለኔ ልዩ ቀኔ ነበር በላቤ ያገኘሁትን ገንዘብ አንድ ሁለት በዬ የምቆጥርበት ለናቴ የገባሁትን ቃል እምፈፅምበት፡፡ እዛው የምሰራበት የምሰራ ቤቲ የምትባል ልጅ ተግባብተን ጓደኛሞች ሆነናል እናም ልክ ደሞዝ እንደተቀበልኩ ሄደን ምጣዱን ገዛን በመኪና አስጭኜ ቤት በር ላይ ቆሜ
"እማ እማ ነይ ውጪ አንዴ?" እናቴን ሰርፕራይዝ ለማረግ አስቤ ነው የጠራኀት
"ምንድነው? ምትክ ምነሆነሻል?" እየተጣደፈች ስትወጣ ደንግጣ ቆመች
"ምንድነው ይሄ ምትኬ"
"እማ ደሞ ምጣድ ነዋ"
እሱንማ አየሁ እኮ ግን የማነው"
"እህህ ላንቺ ነዋ አሰልፊያቸው ይግቡ ዛሬ እኮ ደሞዝ ተቀበልኩ"
ገለል እያለች እልልታዋን አቀለጠችው ደስታዋ ደስ አለኝ የቀረችኝን ትንሽ ብር በእጇ ሳረግላት
"ምትኬ ሴት ነሽ በዚህ ለራስሽ የምፈልጊውን አርጊ ለኔ በቂ ነው የገዛሽው ጌታ ይባርክሽ ሌላ ቃል የለኝም" ገብታ ቦታ አሳየቻቸው ላመጡበት ከፍዬና አመስግኜ ሸኘኋቸው እናቴ ለካ ደስታቸውን መቆጣጠር አቅቷት ለጎረቤቶቿ እየዞረች እያወራች ነበር፡፡
ቤቲ ይሄ ሁሉ ሲሆን በመገረም እና የደስታ እምባ በማንባት እያየችን ነበር
"ብሌን" አለችኝ
"ወዬ" አልኳት አጠራሯ ገርሞኝ እየዞርኩ
"ታድለሽ እናትሽን በቅርብሽ ናት ደስተኞች ናችሁ ሁሌ ተንከባከቢያት" ብላኝ ማልቀስ ጀመረች
"ቤቲ ምንሆነሽ ነው እንዴ በጌታ ተያ"
"ብሌንዬ እናቴን አላቃትም አባቴንም ማሳደጊያ ነው ያደኩት ስወጣ ለመፈለግ ስሞክር ያጣራሁት ነገር ሁለቱም በአደጋ እንደሞቱና ከአደጋው እኔ ስተርፍ የኔ ዘመድ ናት ሚል ባለመኖሩ ለ 2 ወራት ተፈልጎ ፈላጊ ባለመኖሩ ወደ ማደጎ ቤት ተወሰድኩ ከዛም በቃ ፍለጋዬን እዛ ጋር አቆምኩ አሁን ሳያቹ ቀናሁ""ካሁን በኋላ እማዬ እናትሽ እኔም እህትሽ ነኝ በክፋም በደጉም አብሬሽ ልሆን እማ ትሙት ቃል እገባለሁአንቺ እህቴ ነሽ እሺ ቤቲዬ
"እሺ አመሰግናለሁ እሺ ብሌንዬ ወድሻለሁ"
ቀነችንን በደስታ አሳለፍን ስራዬን ወድጄዋለሁ የስራ ባልደረቦቼንም እንደዛው ተግባብቼ ወድጃቸዋለሁ
ዛሬ ስራ ከጀመርኩ 1 ወር ከ15 ቀን ሆኖኛል ደምበኞችን እያስተናገድኩ ነው የአንድ ወጣት የባንክ ደብተር ተቀብዬ ሳይ ገቢ 10000 ብር ይላል እያስገባሁ ቀና አልኩ
"ሰላም ብሌን አዲስ ነሽ መሰለኝ?"
"አዎ ሰላም"
"ብሩክ እባላለሁ ደንበኛ ነኝ ቆንጆ ነሽ ቆንጆ ሴቴችን ማወደስ ወዳለሁ" ስራዬ ስለሆነ ፈገግ ብዬ እየሰማሁት ነው እንደ እውነቱ ከሆነ በጣም ጉረኛ ነው አስጠልቶኛል ከስራ ውጪ ቢሆን ኖሮ ሰድቤው ነበር፡፡ ጨርሼ ቡኩን ስመልስ በእጁ የያዘውን የመቶ ብሮች ኖት እየሰጠኝ
"ጉርሻ ነው ያዢው አለኝ " በሂወቴ እንደዛ ተበሳጭቼ አላቅም ባንክ ቤት ውስጥ ያሉት በሙሉ በሁኔታዬ ተገርመው ዞሩ

ክፍል 4 ይቀጥላል ከተመቻችሁ
#join #share