Get Mystery Box with random crypto!

The Equation Group አሜሪካ አሉኝ ከምትላቸው ሚስጥራዊ የደህንነት ድርጅቶች ውስጥ የCy | Ethio Computer Science

The Equation Group

አሜሪካ አሉኝ ከምትላቸው ሚስጥራዊ የደህንነት ድርጅቶች ውስጥ የCyber operation በማካሄድ እና በአሜሪካ ደህንነት ድርጅቶች የሚፈለጉ ግለሰቦች እንዲሁም ድርጅቶችን አድኖ ለመያዝ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን በእጅጉ የረቀቀ የኮምፒዩተር እውቀትን በመጠቀም በሚዘጋጁ የኮምፒዩተር ቫይረሶች በመታገዝ ስለግለሰቦቹ መረጃን የሚያሰባስብ ቡድን ነው።

ይህ ቡድን ስራው ይሄ ብቻ አይደለም፣ እንደ Kaspersky Labs ገለጻ ከሆነ፣ ይህ ቡድን በIran፣ Russia፣ Pakistan፣ Afghanistan፣ India፣ Syria፣ እንዲሁም በMali በሚጎኙ ግለሰቦች እንዲሁም ድርጅቶች ላይ ከ10000 የበለጠ የሳይበር ጥቃት አድርሷል። ከእነዚህ ጥቃቶች ውስጥ መከሰታቸውን እንኳ ማረጋገጥ የተቻለው የ500ዎቹን ብቻ ነው።

ይህ የሳይበር ቡድን በ2002ዓ.ም የኢራንን የኒውክሌር ፕሮግራም ያሽመደመደውን የStuxnet ቫይረስ ጨምሮ Bad Rabbit, Spy Eye, Ethernal Blue, Duku የተባሉ የኮምፒዩተር እውቀት መጨረሻ የተገለጠባቸው ቫይረሶችን ለመፍጠር የቻለ አደገኛ ቡድን ነው።

ታዲያ ግን ነሃሴ 2016 ላይ አንድ ያልታሰበ ድርጊት ተፈጸመ፥ ራሱን Shadow Brokers ብለው የሚጠራው...

[ክፍል ሁለት ይቀጥላል]