Get Mystery Box with random crypto!

[የቀጠለ] ታዲያ ግን ነሃሴ 2016 ላይ አንድ ያልታሰበ ድርጊት ተፈጸመ፥ ራሱን Shadow Bro | Ethio Computer Science

[የቀጠለ]

ታዲያ ግን ነሃሴ 2016 ላይ አንድ ያልታሰበ ድርጊት ተፈጸመ፥ ራሱን Shadow Brokers ብሎ የሚጠራው የHacker ቡድን የEquation Group መስርያ ቤት Serverኦችን ሰብሮ በመግባት ቡድኑ ከሚጠቀምባቸው ረቂቅ የHacking መሳሪያዎች ውስጥ የWindows ኮምፒዩተሮችን ሰብሮ በመግባት ጥቅም ላይ ይውል የነበረ Ethernal Blue የተባለ tool ለመስረቅ ችሏል።

ቡድኑ በዚህ አላቆመም፥ ይህን ባደረገ በ3 ቀናት ውስጥ የሰረቀውን መሳሪያ ለመግዛት ከፍተኛውን ዋጋ ለሚያቀርብ ማንኛውም ቡድን ለመሸጥ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ፣ ይባስ ብሎም ከመሳሪያው ሽያጭ በቂ ገንዘብ ከሰበሰበ በኋላ መሳሪያውን ማንኛውም የፈለገ ሰው ይጠቀምበት ይችል ዘንድ Github ላይ ለመልቀቅ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ።

እንዳለውም ቃሉን ሳያጠፍ ከወራት ቆይታ በኋላ Ethernal Blue የተባለውን መሳሪያ ለአለም ተደራሽ ይሆን ዘንድ Github ላይ አስቀምጦታል፣ በተጨማሪም ይህ መሳሪያ በአብዛኛዎቹ የኮምፒዩተር ደህንነት ተመራማሪዎች እንዲሁም ሃከሮች ጥቅም ላይ በሚውለው Kali Linux ኦፕሬቲንግ ሲስተም ውስጥ በሚገኝ Metasploit በተባለ የሃኪንግ መሳሪያ ስብስብ ውስጥ እንደ አንድ መሳሪያ ተካቶ ይገኛል።

@ethio_computer_science