Get Mystery Box with random crypto!

#ኡቡንቱ(Ubuntu Operating system) 1980ዎቹ ዩኒክስ ኦፕሬትንግ ሲስተም ብዙ ኮም | Ethio Computer Science

#ኡቡንቱ(Ubuntu Operating system)

1980ዎቹ ዩኒክስ ኦፕሬትንግ ሲስተም ብዙ ኮምፒዩተሮች ይጠቀሙ ስለነበር የተለያዩ ሰዎች የኦፕሬትንግ ሲስተምን ኮድ(source code) ባለቤትነት ጥያቄ በማቅረባቸው የኒክስ ኮዱን ማጋራት አንዲከለከል ተወሰኑ፡፡ ይህን ቀድሞ ያየው ተዋቂዉ የኮምፒዩተር ባለሙያ #ሪቻርድ_ስታልማን የዩኒክስ ኦፕሬትንግ ሲስተም ተመሳሳይ ግለባጭ ለመስራት ወስነ፡፡ በሪቻርድ ስታልማን እምነት ሶፍትዎር መጋራት(share) ምንም ጉዳት አንደሌለው እና የሶፍትዌር ጥራትንም እደሚጨምር ያምን ነበር፡፡ ሪቻርድ ስታልማን የሰራውን ዩኒክስ ኦፕሬትንግ ሲስተም ለማንም ሰው እዲጠቀመው በነጻ ለቀቀው፡፡
በሪቻርድ ስታልማን እና ኮናኪያል ዩኒክስ ኦፕሬትንግ ሲስተም በማሻሻል አንዲሁም ለአንድ ኦፕሬትንግ ሲስተም ከሃርድዌር ጋር ለመግባባት ወሳኝ የሆነው ከርንል በማካተት በ2004 ለመጀመሪያ ግዜ ተለቀቀ፡፡ስሙም #ኡቡንቱ ተብሎ ተሰየመ፡፡ ኡቡንቱ ማለት አፍሪካዊ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “ለሌላው ማስብ” ወይም “ሰብአዊነት” ማለት ነው፡፡ ኡቡንቱ ተወዳጂነት ያተረፈው ወዲያው ነበር ከሌላው ሉኔክስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም #ቀላል እና ለመልመድ #የማያስቸግር በመሆኑ ተወዳጅነትን አትርፏል፡፡ ኡቡንቱ በየስድስት ወር ዝመና(update) ያደረጋል፡፡

ኡቡንቱ ከሌሎች ኦፕሬትንግ ሲስተም #በምን_ይለያል?

ከቫይረስ ጥቃት ነጻ መሆኑ
በፍጥነት ከሌሎቹ የተሻለ በመሆኑ
ድራይቨር መጫን አለመጠየቁ ወይም አለማስፈለጉ
የራም አና የሲፒዩ አጠቃቀሙ የተሻለ በመሆኑ
ለሪሰርች ትልቅ ድጋፍ ስላለው
ለሳይንቲፊክ ጥናት ተመራጭ በመሆኑ

@ethio_computer_science