|| The great wall ! - በ አርሰናል ዝዉዉር ታሪክ ዉስጥ በጣም ብዙ ከተዘገቡ ዜናዎች | ETHIO ARSENAL

Picture 1 from ETHIO ARSENAL 2024-01-24 12:08:43
|| The great wall !

- በ አርሰናል ዝዉዉር ታሪክ ዉስጥ በጣም ብዙ ከተዘገቡ ዜናዎች መካከል የ ጋቢ ማጋሌሽ አንዱ ነዉ ። ጋቢ ማጋሌሽ ከሊል ወደ አርሰናል የሚለዉ ዜና የመጣ ሰሞን ዊሊያም ሳሊባ ወደ አርሰናል አልመጣም ነበር ። እና የዚህን ጀግና ተከላካይ ዩቲዩብ ላይ ስመለከት ሁለቱ ሊኖራቸዉ የሚችለዉን ጥምረት ሳይ በጣም ጓጉቼ ነበር ። የፈረመ ሰሞኑ ለ አስር ዓመት የመሀል ተከላካይ ጥምረት አገኘን ብዬ ፖስት አድርጌ ነበር ።

- ማጋሌሽ ዝዉዉሩ በትክክል በፎቶ ይፋ አልሆነም ፤ አስታዉሳለዉ ምሽት ነገር ላይ በደበዛዛ ሰለፊ ፎቶ ወደ አርሰናል መምጣቱ ተረጋገጠ ። የመጀመሪያዉ ጨዋታ ላይ ማለትም ከ ፉልሀም ግብ አስቆጥሮ አስገረመን ። ወኔዉ ፣ አልሸነፍ ባይነቱ ፣ ሲሳት ያለዉ ቁጭት ደግሞ ለክለብ ያለዉ ፍቅር ልዩ ነዉ ። ጋብሬል ማጋሌሽ አሁን ሊጉ ላይ ብሎም አለም ላይ ካሉ ምርጥ ተከላካዮች ጭምር ተሰልፏል ።

23 -28 ሚሊዮን ፓዉንድ በሚደርስ ብቻ ነዉ የፈረመዉ !


"SHARE" . @ETHIO_ARSENAL
ETHIO ARSENAL

ETHIO ARSENAL

@ethio_arsenal
344 ተመዝጋቢዎች
ያልተመደበ ምድብ
–The Best Arsenal Football Club Telegram Channel in Ethiopia. –በኢትዮጵያ ትልቁ የአርሰናል ቴሌግራም ቻናል ነው። ስለ አርሰናል አዳዲስና ትኩስ ...