2022-08-31 09:55:09
ነሐሴ 25 ቀን 2014 ዓ.ም
በፈተና ነጥራ የወጣች ሀገር ኢትዮጵያ!!
ሀገራችን ኢትዮጵያ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ፈተናዎች ያጋጥሟታል። ኢትዮጵያን ፈተናዎች አላዳከሟትም ይልቁንም ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሆና ወደፊት እንድትቀጥል አበርትቷታል።
ኢትዮጵያ ወርቅ ነች። ወርቅ በእሳት ነጥሮ አምሮና ደምቆ እንደሚወጣው ሁሉ ኢትዮጵያም በፈተናዎች አልፋ ለዘመናት ታፍራና ተከብራ ኖራለች ትኖራለችም።
ኢትዮጵያ ፈታኞቿ የውጭ ጠላቶቿ ናቸው። እነዚህ ኃይሎች ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ሀገራችንን ፊት ለፊት ገጥመው ማሸነፍ እንደማይችሉ ከታሪክ መዝገብ የተረዱ በመሆናቸው በባንዳና ተላላኪዎች አማካኝነት ፍላጎታቸውን ማሳካት ይፈልጋሉ።
በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የሚጋለበው አሸባሪው የህወሓት ቡድንም እነሱ ያልተሳካላቸውን ሀገር የማፍረስ ህልምቸውን ተቀብሎ መቃዠት ከጀመረ ሰምበትበት ብሏል ብቻ ሳይሆን ከርሟል።
ኢትዮጵያን ፊት ለፊት ገጥመው የሆኑትን እና የሚሆኑትን የሚያውቁት የውጭ ጠላቶቻችን የወስጥ አንድነታችን ተበጣጥሶ አሸባሪውን ለማንገስ ዳክረዋል።
ወርቅ በእሳት ነጥሮ ወርቅ እንደሚሆነው ሁሉ ኢትዮጵያም በፈተናዎቿ ነጥራ የምትወጣ እንጂ ጠላቶቻችን እንደሚያስቡት የምትፈረካከስ ሸክላ አይደለችም።
የጀግኖች አባቶቹ ልጆች የሆነው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን የተረከባትን ሉአላዊ ሀገር ከጠላት እና ከባንዳ ተከላክሎ ለቀጣዩ ትውልድ የማሸጋገር ታሪካዊ ኃላፊነት ያለበት ኃይል ነው።
ለዚህም ሠራዊታችን የገጠመንን ጠላት በማንኛውም ጊዜ እና ሠአት በመንግስት በሚሠጠው አቅጣጫ መሠረት ጠላትን በማደባየት ታሪካዊ ኃላፊነቱን ይወጣል።
#ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች!!
316 views06:55