Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመስጠት ታብሌቶች ካልደረሱ ሌሎች አማራጮች እንደሚጠቀም መንግስት | ሰበር !!

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመስጠት ታብሌቶች ካልደረሱ ሌሎች አማራጮች እንደሚጠቀም መንግስት አስታወቀ!!

በሚቀጥለዉ አመት በኦንላይን ይሰጣል ለተባለዉ ሀገር አቀፍ ፈተና ይገባሉ የተባሉ 1 ሚሊዮን ታብሌት ኮምፒውተሮች በወቅቱ ካልደረሱ ሌሎች ምርጫዎችን መንግስት ይከተላል-ጠ/ሚ አብይ

በ2015 ዓ.ም የሚሰጠዉ ሀገር አቀፍ ፈተናን ዲጂታል በሆነ መንገድ በኦንላይን ምዘናዉን ለመስጠት ታቅዶ እንደነበር ይታወሳል። ለዚህም 1ሚሊዮን የሚሆኑ ታብሌት ኮምፒውተሮች ወደ ሀገር ይገባሉ ተብሎም ነበር።

ጠ/ሚ አብይ ይህን በተመለከተ በሰጡት ማብራርያ ያለዉን ስርቆት ለማስቀረት ሲባል ፈተናዉን ዲጂታላያዝ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል። ለዚህም 1ሚሊዮን ታብሌት ኮምፕዩተሮቹን ከቻይና መንግስት ጋር በመሆን ለማስገባት እየተሰራ እንደነበር አስታዉሰዋል። ሆኖም በኮቪድ 19 ቫይረስ ምክንያትም አምራች ድርጅቱ ስራዉን በተያዘለት ግዜ ማጠናቀቅ አለመቻሉን አስታዉቀዋል።

በ2015 ለመስጠት የታቀደዉ ፈተናዉ ፤ በቂ ዝግጅት ስለተደረገ ታብሌት ኮምፒውተሮቹ በተያዘላቸዉ ግዜ ከደረሱ ፈተናዉ ይሰጣል ብለዋል። ሆኖም ታብሌቶቹ በግዜዉ ካልደረሱ መንግሰት ሌሎች ምርጫዎችን እንደሚጠቀም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል።

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  @Ethiiostudents_bot

        Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students  
╚═══════════╝