Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለ 62 ወለል ህንፃ ሊያስገነባ ነው። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል | Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለ 62 ወለል ህንፃ ሊያስገነባ ነው።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለ 62 ወለል የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ለመገንባት የሚያስችለውን ስምምነት በዛሬው ዕለት መፈራረሙን ገልጿል።

በ197 ሺህ 800 ካሬ ሜትር መሬት ላይ የሚያርፈውና 445 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በጀት የተመደበለት ይህ ህንጻ ሲጠናቀቅ 327 ነጥብ 5 ሜትር ርዝመት ይኖረዋልም ተብሏል፡፡

የዲዛይንና የቁጥጥር ሥራውን የሚያከናውነው ዳር አል ሃንዳሳህ ሼር እና ፓርትነር ኩባንያ (Dar Al Handasah Shair and Partners) መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል።

ማስታወሻ : በመዲናዋ ትልቁ ህንጻ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ያስመረቀው ባለ 48 ወለል ህንጻ ነው። ከዚህ በተጨማሪ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ባለ 65 ወለል ህንጻ፤ እንዲሁም የአቢሲኒያ ባንክ በበኩሉ 60 ወለል ህንጻ እንደሚገነቡ መግለጻቸው ይታወሳል።

@etconp