Get Mystery Box with random crypto!

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የቤተ መንግሥት ግንባታ በአዲስ አበባ ሊጀመር ነው:: በአዲስ | Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የቤተ መንግሥት ግንባታ በአዲስ አበባ ሊጀመር ነው::

በአዲስ አበባ ከተማ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኝ ከስድስት ሄክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ፤ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ቤተ መንግሥት ሊገነባ ነው።

በግንባታው ማስጀመሪያ መርሃግብር በዛሬው ዕለት የተከናወነ ሲሆን፤ በመድረኩም የክልሉ ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሚያና የፌዴራል አመራሮች፣ አባ ገዳዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና የሲንቄ እናቶች ተገኝተውበታል።

የቤተ መንግሥቱ አጠቃላይ የግንባታ ሥራ በኹለት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ ዕቅድ የተያዘ ሲሆን፤ ግንባታው ኹለት ምዕራፎች እንዳሉትም የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

የታቀደውን ቤተ መንግሥት ለመገንባት ከቻይናው ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (CCECC) ጋር የውል ስምምነት የፈጸመ ሲሆን፤ ኩባንያውን በተያዘለት ጊዜ ውስጥ ግንባታውን ለማጠናቀቅ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታውቋል።

ለቤተ መንግሥቱ ግንባታ የተመደበው ዋጋን አስመልክቶ እስከአሁን የተገለጸ ነገር የለም።

@etconp