Get Mystery Box with random crypto!

┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓ '. #ሀፍሲ '. ✎ፀሐፊ፦ መግፊራ ቢን | 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖

┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
". #ሀፍሲ ".
✎ፀሐፊ፦ መግፊራ ቢንት ፉላን
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
#እውነተኛ_ታሪክ

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
#ክፍል_አምስት ʕ➎ʔ
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

ሀኑ አንዳንዴ በህይወትሽ ጥሩ ይሆናሉ ብለሽ አስበሽ የምትሰሪያቸው ነገሮች ወደ መጥፎ ይቀየራሉ፤ ታድያ መጥፎነታቸው ባንቺ ህይወት ውስጥ ብቻ አይደለም፤ የምትወጃቸውን ሰዎች ሁሉ ይጎዳብሻል፤ እስከህይወትሽ ፍፃሜ ድረስ ስትፀፀቺበት እና ስታፍሪበት ትኖሪያለሽ፤ ማንነትሽን ያሳጣሻል፤ ትላንት ላይ ምንም አይፈጥርም ብለሽ በራስሽ ወስነሽ ጥሩ የሰራሽ መስሎሽ ያደረግሽው ነገር ወደታች ይቀብርሻል። እኔም ጋ የሆነው ይሄ ነው ሀኑ" እንባዋ ይወርዳል ውስጧ በፀፀት እየተቀጣ እንደሆነ በአነጋገሯ ታስታውቃለች........................
"ትምህርት ቤታችን ውስጥ አንድ በጣም ቀልቃላ እና ቆንጆ ልጅ ነበረች፤ እና ሰሚር በጣም ይወዳት ነበር፤ እናም ይህን ደሞ ለኔ አልነገረኝም፤ እናልሽ የሆነ ቀን ላይ በጓደኞቹ ግፊት ይሄድና እንደሚወዳት ምናምን ይነግራታል፤ እሷም በጣም ሳቀችበት፤ ሰሚር ስትስቅ ግራ ገባው ጥሏት ሊሄድ ቢፈልግም ግን መልሷን መስማት ስለነበረበት አጠገቧ በዝምታ ቆመ። ልጅቷ የመጀመርያው ጥያቄዋ "ምነው ከሀፍሲ ጋር ተፋታቹ እንዴ? ነበር፤ ግራ ገባው ምን ይመልስላት? ከሀፍሲ ጋ ኮ...... አላስጨረሰችውም "አንተ ግን ትንሽ አይደብርህም? እሷ ለጠየቃት ላልጠየቃት ሁላ ባሌ ነው እያለች ታወራለች፤ አንተ ግን እሷ ላይ ልትደርብባት ሌላው ይቅር እህት የለህም? እሷ ብትሆንስ ብለህ አታስብም? ብላ ሰሚርን በጥፊ አላትማው የተቀመጠበት ጥላው ሄደች። በቃ ምን አለፋሽ ሀኑ 9 ሰዐት ወደ ት/ት ቤት ተለቀን ልንሄድ ስጠብቀው ስጠብቀው አልመጣም ምን ሆኖ ነው ብዬ ጓደኞቹን ስጠይቅ ቀድሞ እንደሄደ ነገሩኝ። አሞት ይሆናል ብዬ ስከንፍ ሄድኩልሽ። ቤት ስሄድ የለ፤ ከት/ት መቶ ጓደኞቼ ጋር ብሎ ሄዷል አሉኝ እናቱ፤ እስኪመጣ ጠበኩት ያለወትሮው አምሽቶ መጣ ግን ሊያናግረኝ ፍቃደኛ አልነበረም፤ በ1 ነገር ተበሳጭቶ ይሆናል ብዬ ተውኩት ሲነጋም ት/ት ቤት ጥሎኝ ሄደ ት/ት ሄጄ ላናግረው ብሞክርም አልቻልኩም ግን ት/ት ቤቱ ሙሉ ይወራ የነበረው ስለ እሱ ነበር። ሰሚር ለምን እንደኮረፈኝ ገባኝ ግን ሳስረዳው ይረዳኛል ብዬ ስላሰብኩ አሁንም ጠበኩት ግን ጥሎኝ ሄዷል። ወደቤት ሄጄ ሳናግረው ሊያናግረኝ እንደማይፈልግ አስረግጦ ነገረኝ። ላስረዳው ብሞክርም ግን አልሰማም አለኝ! ንዴቱ ይልቀቀው ብዬ ተውኩት ሳምንት ሙሉ ዝም ተባባልን የሴሚስተር እረፍት ስለነበረ እኔም አንቺ ጋር መጣው ከዛም የሆነ ቀን ላይ "ናፈቅሽኝ በቃ ነይ" የሚል ቴክስት ላከልኝ ታስታውሻለሻ አሁኑኑ መሄድ አለብኝ ብዬ ስቀውጠው፤ ሁለቱም ጊዜውን አስታውሰው ፈገግ አሉ ካንቺ ጋር መጥቼ እቤት ከመግባቴ በፊት አገኘሁት ይሀው ዛሬ እኔና አንቺ የተቀመጥንበትን ቦታ ለመጀመርያ ጊዜ ያወኩት የዛኔ ነው ፈገግ....... ላጠፋሁት ጥፋት ሁላ እያለቀስኩ ይቅርታ ጠየኩት እንደዛ ያልኩበትንም ምክንያትም አስረዳሁት፤ ይቅርታዬን ተቀበለኝ ግን ሁለተኛ እንደዚአይነት ስህተት እንዳልፈፅም አስጠነቀቀኝ፤ እኔ ላንቺ ወንድምሽ እንጂ በፍፁም ባልሽ መሆን አልችልም፤ ደሞ አልሆንም! መቼም ቢሆን እንዳታስቢው ደሞ ወንድም ባል አይሆንም!" ሲል አስጠነቀቀኝ በሰዐቱ እሱ ለኔ እንደነ አህመድ ስለነበር ምንም አልመረለኝም ጥፋቴን እንደማልደግም ቃል ገባሁለት። ሀኑ ሰሚሩ በኔ ምክንያት ባጣት ልጅ ብዙ ተጎዳ ትምህርቱንም አቆመ፤ ይሀን ማቀው ግን እኔ ብቻ ነበርኩ በሰዐቱ ለእናንተ ስራ መጀመር አለብኝ ብሎ አሳምኗቹ ስራ የጀመረው ለእናቱ ሳይሆን በኔ ስህተት ነበር ..... ብቻ ብዙ ነገር አለፈ፤ የኔና ሰሚር ቅርርብ በጣም እየጠበቀ መጣ ትምህርቱን ቢተወዉም እኔን ሊያደርስ ይመጣ ነበር 12ኛ ክፍል ጨርሼ ጊቢ ውጤት ሲመጣልኝ ከነአህመድ ጋ ተባብሮ ያስቀረኝም እሱ ነው። ቢሆንም ግን ኮሌጅ እየመጣ ያዳብረኝ ነበር፤ እስክትለምጂ እያለ ሰሚር ከማንም በላይ ይንከባከበኛል፤ አባቴ ሲሞት የጥንካሬዬ ምክነያት እሱ ነበር፤ ለኔ ያለው ቦታ የተለየ ነው።
በሀዘን አቀረቀረች እና ምን ተፈጠረ? እንደዚ ሚያስብልሽ ከሆነ ለምን ያንቺ መሆን አቃተው?.....
እውነትም ሰሚርን የሀፍሳ ለመሆን ምን ከለከለው ይወዳት የለም.........?

╬╬═════════════╬╬
#ክፍል_ስድስት_የመጨረሻው_ክፍል ይቀጥላል
╬╬═════════════╬╬
@eslamik_tube
@eslamik_tube
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤