Get Mystery Box with random crypto!

┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓ '. #ሀፍሲ '. ✎ፀሐፊ፦ መግፊራ ቢን | 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖

┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
". #ሀፍሲ ".
✎ፀሐፊ፦ መግፊራ ቢንት ፉላን
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
#እውነተኛ_ታሪክ
┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒
. በ @eslamik_tube የተዘጋጀ .
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
#ክፍል_ስድስት_የመጨረሻው_ክፍል
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

ሰሚር እና እኔ ብቻችንን ሆነን ለሚያየን ሰው በጣም ምንፋቀር ነው ምንመስለው፤ ግን እንደዛ አደለም! ሰሚር እኔን የሚያፈቅር ልብ የለውም፤ በቃ ከዛች 11ኛ ክፍል አፍቅሯት ከገፋችው ቡሀላ ሴት ልጅን ማፍቀር አልችልም እያለ ይነግረኛል፤ "አንቺ ግን እንደምታፈቅሪው በምን እርግጠኛ ሆንሽ ሀፍሲ?"
ሀኑዬ የሆነ ጊዜ ምን ሆነ መሰለሽ ሰሚር ለስራ ብሎ ከጓደኞቹ ጋር ወደ አዳማ ለ5 ቀን ሄደ ፤ እና በጣም ብዙ ፎቶወች ይልክልኝ ነበር፤ ከሴት ጋ የተነሳውን ምናምን በቃ እሱን እያየው እኔ ደሞ ቅጥል ማለት ጀመርኩ፤ ይናፍቀኝ ጀመር፤ ጭራሽ ያቀፋትን ሴት መሆንን መመኘት ጀመርኩ፤ እሱ ሚልክልኝ የትኛዋን ለሚስትነት ትሆናለች? እያለ ነበር። እኔ ግን ሴቶቹን ሁላ ጠላውሀቸው፤ አግኝቼ ብገላቸው ሁላ ደስተኛ ነበርኩ። ቀን እና ማታ ስለእሱ ማሰብ ጀመርኩ፤ አሁን ከየትኛዋ ጋ ይሆን? አሁን ምን እየሰራ ይሆን? ሀሳቤ ሁላ እሱ ሆነ! 5ቱ ቀን 500 አመት ሆነበኝ። ከነዛ ሴቶች ተላቆ ሚመጣበት ቀን ናፈቀኝ! እራሴን ተጠራጠርኩት አፈቀርኩት እንዴ? ብዬ ስለፍቅር የሚያወሩ ንግግሮችን ሰማው፤ መፅሀፎችን አነበብኩ፤ ከዛም በቃ ከሱ ፍቅር እንደያዘኝ እርግጠኛ ሆንኩ። ግን አልከፋኝም ነበር፤ ነገር ግን ለማንም ሳልናገር መጀመርያ የሱን መልስ መስማት አለብኝ ብዬ ወሰንኩ ....................
"ሰሚርን በመጣ በማግስቱ ምሳ ጋበዝኩት እዚው ቦታ ላይ እዛኛው ቤት እጇን ጠቁማ መናፈሻ ውስጥ ካለው አንድ ምግብ ቤት ለሀኑ አሳየቻት። ምግቡን በላንና እዚችው ቦታ መጥቼ አዳማ እያለ ሳስብ የነበረውን ነገር ሁላ ነገርኩት፤ ሀኑዬ ሰሚር እንደሚወደኝ እርግጠኛ ብሆንም ግን እንደሚያፈቅረኝ ግን እርግጠኛ አልነበርኩም፤ ቢሆንም ግን ከሱ መጥፎ መልስን አልጠበኩም ነበር። ምክንያቱም ለኔ ሚያደርገውን ነገር ማንም አያደርግልኝም ነበር፤ ሰሚር ተናግሬ ስጨርስ ፊቱ ተቀያየረ፤ "ስህተትሽን ልትደግሚው ነው አይደል ሀፍሲ? ቃልሽን አጠፍሽ አይደል?" አንባረቀብኝ፣ ደነገጥኩ፣ መሬት ተሰንጥቃ በዋጠችኝ ብዬ ተመኘው፤ ከተቀመጠበት ምንጭቅ ብሎ ተነሳና እንሂድ አለኝ ተነሳው፤ ምንም ሳንተነፍስ ወደቤት ሄድን፤ መሸ እንቅልፍ መተኛት አልቻልኩም ስገላበጥ ለሊቱ ተጋመሰ ልክ 6 ሰዐት ሲል የስልኬ የመልክት ድምፅ አቃጨለ ሰሚር ነበር እንዲህ ይላል "ይሀውልሽ ሀፍሲ ቀን የተፈጠረውን ነገር በቃ እንዳልተፈጠረ እንቁጠረው እርሺው እኔ አንቺን መውደድ እንጂ ማፍቀር በፍፁም አልችልም። አንቺ ማግባት ያለብሽ ሀብታምና ቆንጆ ወንድ ነው፤ ቤተሰቦችሽም ሚፈልጉት ጥሩ ቦታ እንድትወድቂ ነው፤ እኔ ደሞ ላንቺ አልሆንም። ግን አንድ ነገር ልንገርሽ ለማንም የማትናገሪ ከሆነ እና በኔ እርግጠኛ ከሆንሽ አንቺ እንዳትጎጂ ፍቅር እንጀምራለን" ይላል። በሰዐቱ ሚታየኝ እሱን አለማጣት ስለነበረ ምንም ሳላቅማማ በሀሳቡ ተስማማው ፍቅረኝነት በጀመርን የመጀመርያው ሰሞን ሰሚር ያፈቅረኛል ብዬ እስከምል ድረስ ለኔ ይጠነቀቅልኝ ነበር። ግን ሀኑ ከሆነ ጊዜ በውሀላ ተቀየረ፤ በቃ አለው የለሁም አይነት ጨዋታ መጫወት ጀመረ፤ እኔጋ ሲመጣ እንደፍቅረኛ አክት ያደርጋል፤ ቤተሰቦቼ ጋ ደሞ ሌላ ሰው ይሆንብኛል፤ ደስ ሲለው ላፈቅርሽ አልችልም እያለ ይሰብረኛል፤ አገባሻለው ብሎኝ ፈንጥዤ ሳልጨርስ ለእናቱ እንደማያገባ በኔ ፊት ይነግራታል፤ ስለእኔ ስሜት አይጨነቅም፤ ሀኑ ልተወዉ ብፈልግም ግን አልቻልኩም፤ ከሱ መለየትን እፈራለው፤ አለ ስለው የለም፤ የለም ብዬ ተስፋ ልቆርጥ ስል ይመጣል፤ በመኖር እና ባለመኖር ውስጥ አሰቃየኝ፤ ሀኑ ይለወጣል ብዬ ስጠብቀው ይሀው 5ወራት አለፉ፤ እሱ ግን ብሶበታል፤ ወይ ከሱ ወይ ከቤተሰቦቼ ወይ ከትምህርቴ ሳልሆን እንሜዬ አለቀ፤ ቆይ ምንድነው ጥፋቴ ማፍቀሬ ነው ወይስ ሰሚር እየተበቀለኝ ነው ለመጀመርያ ጊዜ ያፈቀራትን ሴት በኔ ምክንያት ስላጣት አሁን እኔን እየተበቀለ ነው ምንድነው ሀኑ ግራ ገባኝ እኮ
"ለምን በግልፅ የሚሰማሽን አታወሪውም ሀፍሲ?"
አጣዋለው አ፣ ይሄድብኛል፣ ይርቀኛል፣ ከዛ እኔ እንዴት እኖራለው..............ተንሰቀሰቀች
ሀናን ምን ማለት እንዳለባት ግራ ገብቷታል
ተይው አትላት ነገር ምታጣት መሰላት እሱን ትታ መኖር ምትችል አልመሰላትም .....................
ጠብቂው አትላት ነገር ምኑን ተማምና የማያፈቅራትን ወንድ ታስጠብቃት .............
ታሪኩ አለቀ የሀፍሲ ህመም ግን ይቀጥላል .....

⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
#ተፈፀመ || #The End
╬╬═════════════╬╬

╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
@eslamik_tube
@eslamik_tube
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧