Get Mystery Box with random crypto!

:::::::መንታ መንገድ::::::: ክፍል 26 fuad seid . . ራሴን ከአንድ ሰዓት ለ | 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖

:::::::መንታ መንገድ:::::::

ክፍል 26

fuad seid
.
.
ራሴን ከአንድ ሰዓት ለሚበልጥ ጊዜ አላዉቅም ነበር። አይኔን
ስገልጥ ነጭ አምፖል ሰማያዊ ኮርኒስ ላይ ይታየኛል። ወዲያዉ
ቀና ስል ከፊት ለፊቴ ሰዒድ እና ቁርዓን ሲቀራብኝ የነበረዉ ሰዉዬ
እየተመለከቱኝ ነበር።
ቁርዓን ሲቀራብኝ የነበረዉ ሰዉ ወዲያዉ ጌታዬን እንዳመሰግን
አዘዘኝ። አመሰገንኩ። ወዲያዉ ወደ ጆሮዬ ተጠግቶ ለስግደት
ጥሪ የሚደረገዉን አዛን እያደረገ የማጅራቴን ደምስሮች በጣቱ
ነካካቸዉ።
"ሴቶች በጣም ይወዱህ ነበር?" አለኝ ኡስታዙ ሰዒድ አጠገብ
እየተቀመጠ
"እንደዛ ነገር" አልኩት።
"ያይኔአበባ የምትባል ሴት ታዉቃለህ?" አለኝ አይን አይኔን እያየ።
"አዎ ዩኒቨርሲቲ ስማር የምጠቀምበት ምግብ ቤት አስተናጋጅ
ናት።" አልኩት።
ሰዒድ በግርምት አንገቱን ነቀነቀ። ኡስታዙ "እዛ ቤት በጣም
ጣፍጦህ የበላህበት ቀን ትዝ ይልሀል?" አለኝ።
እንደድንገት አንድ ቀን የበዓል ስጦታ ብላ ያይኔአበባ የሰጠችኝ
ምግብ ትዝ አለኝ። እንደዉም ብቻዬን ዶርም ነበር የበላሁት።
ኡስታዙ ሌሎች ጥያቄዎችንም ጠይቆኝ ከመለስኩለት በኋላ
ድግምቱ የተሰራብኝ በያይኔአበባ እንደሆነ ነገረኝ። ያይኔአበባ
ወዳኝ እንደነበር ግን ልትፎካከራቸዉ በማትችላቸዉ ቆንጆ ሴቶች
ተከብቤ የነበረ በመሆኑ ድግምት እንዳሰራችብኝ ራሴን
በሳትኩበት ሰዓት ዉስጤ የነበረዉ ጋኔን መናገሩን አረዱኝ።
ኡስታዙ አሁን በፈጣሪ ፈቃድ ድግምቱ መክሸፉንና ዉስጤ
የነበረዉ መጥፎ ስሜትም እንደሚወገድ አበሰረኝ። በሀይማኖቴ
መጠንከር እንደሚኖርብኝ መክሮ ከግብረስጋ ግንኙነት በፊት
ላደርጋቸዉ የሚገቡ ነገሮችን መከረኝ። .
በተፈጠረዉ ነገር እኔም ሰዒድም ተገርመናል። መኪና ዉስጥ
እንደገባን ሰዒድ "በል እስኪ ዛሬ ሂድና ሞክራት እና ጉዱን
እንየዉ!" አለኝ እየሳቀ። እዉነት ለመናገር በጣም ቅልል
ብሎኛል።
.
ማታ ቤት ስገባ ሀዩ አኩርፋ መጅሊሱ ላይ ተቀምጣለች። ደሞ
ምን ተፈጠረ? "ሀዩዬ ምን ተፈጠረ?" አልኳት ከጎኗ
እየተንበረከክኩ።
"አክረሜ ልዉለድልህ ፍቀድልኝ!" አለች እያለቀሰች። የአልጋ ላይ
ፀባዬ እስኪስተካከል ላለመዉለድ ወስኜ መድሀኒት እንድትወስድ
አዝዣት ነበር። አይ ሀዩ! ከነዚህ የአልጋ ላይ ፀባዬ ምንም
ሳትጠላኝ ልትወልድልኝ መጓጓቷ የፈጣሪ ስጦታ እንደሆነች
እንዳስብ አደረገኝ። ፈገግ አልኩና "አላህ ካለ ነገ ጠዋት
መልሴን እነግርሻለሁ!" አልኳት ዛሬ ማታ ሊፈጠር የሚችለዉን
ሰላማዊ ለሊት ተስፋ እያደረግኩኝ።
.
ማታዉን ኡስታዙ በነገረኝ መልኩ ግንኙነት ከመፈፀማችን በፊት
ሰግጄ ፀሎት አደረስኩ። ከዛም የሀዩ ጭንቅላት ላይ መዳፌን
አስቀምጬ ጌታዬን ለመንኩ። ዉስጤ በእርጋታ ተሞልቷል።
ሀዩን ሳምኳት ፣ እጄ ጥፊ እንዳይቀድመዉ ፈርቼያለሁ።
እየተሳሳምን በስሜት ጠፋን። እጆቼ ሰዉነቷ ላይ ተንሸራሸሩ።
ልክ እንደሰዉ ተገናኘኋት። ሀዩ ፊቷ በእርካታ ተሞልቶ እየሳቀች
"ጌታዬ እንደማያሳፍረኝ አዉቅ ነበር።" አለችኝ። የረዥም ጊዜ
ፀሎቷ ይሄ ነበር መሰለኝ። ሁለታችንም መድገም ፈለግን! ሀይል
አሰባስበን ደገምነዉ። እርካታ ጣራ ነካ! ማመን ከበደኝ።
የምድርን ጣፋጩን ነገር በእርጋታ ማጣጣም ቻልኩኝ። ሀዩ
እቅፌ ዉስጥ ቀለጠች። ፍልቅልቅ እያለች "አፈቅርሀለሁ።"
አለችኝ። ጌታዬን አመስግኜ ሀዩን እቅፍ አድርጌ ተኛሁ።
.
በነጋታዉ ጠዋት ሀዩ ከእንቅልፍ እንደተነሳን የወሰደችዉ
የመጀመሪያዉ እርምጃ የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒኖችን መጣል
ነበር። አሁን ልጅ ያስፈልገናል። ጠዋቱን ሰዒዶ ደወለና "እ
ጄኪጃን አደብ ገዝተህ አደርክ ወይስ?" አለኝ።
"ኧረ አልሀምዱሊላህ ዛሬ ጥፍጥናን አጣጣምኩት። አሁን ከልቤ
እንድትቀምሰዉ ተመኝቼልሀለሁ።" አልኩት።
ተገናኝተን ስለጋብቻዉ ለማዉራት ተቀጣጥረን ስልኩን ዘጋዉ።
ሀዩን በሙሉ አይኔ ለማየት ደፈርኩ። ግንኙነት የፈፀምን ለሊት
ያዉ ስለምመታት ጠዋቱን ቀና ብዬ ላያት በጣም ነበር
የምሸማቀቀዉ። ጠዋት ቁርስ እኔ ካልሰራሁ ብላትም
ከለከለችኝ። ሁኔታዬ ሁሉ እያሳቃት ነዉ። ወንድነቴ ልኩን መያዙ
ከሀዩ ጋር የተሻለ ቅርርብ እንዲኖረኝ አደረገኝ።
.
ጠዋቱን ሀዩን ወደ ቢሮዋ አድርሼያት እኔ ወደ ስራ ሄድኩ።
የራሄል ሆቴልን ጉዳይ በተመለከተ በዋናነት እየመራችዉ ያለችዉ
ሀዩ ናት። አሁን ግንባታዉ ተጀምሯል። ሀጅራም አዲስአበባ ሆና
ስራዉ እንዲቀላጠፍ ለማድረግ እየጣሩ ነዉ። እስክንድር አዲስ
ፍቅረኛ ይዟል። እስክንድርን ካየሁ ሁሌም ራሄል ትዝ ትለኛለች።
አሁን እንኳ ሀዘኔ በጣም ደብዝዟል። ግን በጣም የገረመኝ
የተሰራብኝ ድግምት ከዝሙት እኔን ለመታደግ ምክንያት መሆኑ
ነዉ። ከራሄል ጋር ያደርን ለሊት ስሜቴ ሲግል በጥፊ መታኋት
እና አልጋ ላይ ተዘረረች። እዛዉ እንዳለች ልገናኛት ወደ አልጋዉ
ስሄድ እንደዉም አብሬያት መተኛት ያልፈለግኩ መስሏት
ተፈናጥራ ተነሳች። ለመጥፎ የተደረገብኝ ለጥሩ ጠቀመኝ።
ምንም የስድስት ወሩ የስቃይ ጊዜ ባይረሳም ማለት ነዉ። ለሀዩ
ትዕግስት ግን ምድር ላይ የሚመጥነዉ ሽልማት አላገኘሁም።
.
ጊዜዉ ሄዶ የሰዒዶ እና የኢማን ኒካህ ደረሰ። ደስ በሚል ስነ
ስርዓት የኒካህ ስነ ስርአቱ ተደረገና ከሁለት ቀን በኋላ ሰርጉ
ተደገሰ። ሚዜ ነበርኩኝ። በጣም ደስ የሚል ነበር። የሰርጉ ቀን
ማታዉን ሆቴል እንዳደረስናቸዉ ፈገግ ብዬ "በል ፈረስ ያደርሳል
እንጂ አይዋጋም!" አልኩት።
ሰዒዴ ንግግሬን ጠምዝዞ "ኧረ እኛ ተዋጊ አንፈልግም!" አለኝ
እየሳቀ። በጥፊ የሚማታ አንፈልግም ማለቱ እንደሆነ እኔናእሱ
ተግባብተናል።
.
ጊዜዉ ሄዶ የሀዩ ሆድም ገፋ! እየደከማት ስትቸገር የሷን ስራ
ከነሀጅራ ጋር እየተደጋገፍን ለመሸፈን ሞክረን እሷ ቤት
እንድታርፍ አደረግን። ሀዩዬ ስታረግዝ አንዳንድ የፀባይ
መቀያየሮች ቢስተዋሉባትም እንደምንም ታግሼ ተንከባከብኳት።
አንዳንዴ ለአይኗ ሁሉ አስጠላታለሁ። አንዳንዴ ድብርት በጣም
ይጫጫናታል። የእርግዝናዉ ፀባይ እንደሆነ ስለገባኝ ምንም
ሳልበሳጭ የምትፈልገዉን ሁሉ ለማቅረብ ሞከርኩ።
.
ሀዩ ዘጠነኛ ወሯን ከያዘች በኋላ ብዙም ከሀዩ ቤተሰቦች ቤት
አልጠፋም ነበር። ቢሮ ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮችን አስተካክዬ ወደሀዩ
ወላጆች ቤት እመለሳለሁ። ከሀዩ ጋር ግንኙነት መፈፀም ካቆምን
ሁለት ወር ሆነን። የእዉነት አግኝቶ ማጣት ከባድ ነዉ። ወንድነቴ
ሀዩን አምጣ ብሎ ሊገለኝ ምንም አልቀረዉም። ገና ወልዳ ደሞ
የወሊድ ደም እስከሚቆም ግንኙነት እንደማንፈፅም ሳስበዉ
ሰቀጠጠኝ። የሀዩ ገላ ናፍቆኛል።
የሀዩ ፅንስ በጣም ስለገፋ ወደ ቤተሰቦቿ ቤት ሄዳ እናቷ በጣም
እየተንከባከቧት ነዉ።
ጁምዓ(አርብ) ጠዋት ላይ መግፊራ ደወለችልኝ።
"እሺ እጩ አክስት!" አልኩ ስልኩን አንስቼ
"እጩ አባት! ሚስትዎ እያማጠች ነዉ። ኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል
እየሄድን ስለሆነ ቢመጡ!" አለችኝ።
መግፊ ቀልዷናምሯ አይለይም። "መግፊ እስኪ ወላሂ በይ!"
አልኳት።
ወዲያዉ ስልኩን ወደ ሀዩ አስጠግታ ስታምጥ አሰማችኝ። መኪና
እንደዚህ በፍጥነት መንዳት እችል ነበር እንዴ? በሀያ ደቂቃ
ዉስጥ ሆስፒታል ደረስኩ። መግፊራ ጋር ደዉዬ ወጥታ ይዛኝ
ገባች።
ሀዩ የማዋለጃ ክፍል ዉስጥ ናት። መግባት እንደማልችል
ተነግሮኝ በር ላይ ከነመግፊር ጋር ተቀመጥኩ። ደስ የሚለዉ
አዋላጆቹ ሴቶች ናቸዉ። ወንድ የሚስትህን ብልት እየነካካ
ሲያዋልዳት በጣም ይቀፋል። በተቻለዉ መጠን ሴቶች ስራዉን
በፍጥነት ሊቆጣጠሩት ይገባል።
የሀዩ የስቃይ ድምፅ አልፎአልፎ ይሰማኛል። ሀዩ ስትሰቃይ እኔን
አመመኝ።

ይቀጥላል.......

ይቀላቀሉን

@eslamik_tube