Get Mystery Box with random crypto!

፡፡፡፡፡፡፡መንታ መንገድ፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ክፍል 27 ፀሀፊ fuad seid ለሰኢዶ መንገድ ላ | 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖

፡፡፡፡፡፡፡መንታ መንገድ፡፡፡፡፡፡፡፡፡

ክፍል 27

ፀሀፊ fuad seid

ለሰኢዶ መንገድ ላይ እያለሁ ደውዬ ነግሬው ስለነበር ደርሶ ከኛ ጋር ተቀምጧል፡፡ የሀዪየ እያንዳንዷ ጩኸት በጣም አመመኝ፡፡ ከአይኔ እንባ ፈሠሠ፡፡ "ኧረ በፀጋጋ አይለቀስም! አላህን
ፍራ!" አሉኝ የሀዩ እናት። ሰዒዶ ከክፍሉ ራቅ ብሎ ወዳለ
መቀመጫ ወሰደኝ። ሰዒድ እያየኝ ይስቃል። "ልጅም አባትም
አልቅሳችሁ እንዴት ይሆናል!" አለኝ እየሳቀ!
ንግግሩ እያሳቀኝ "እሱን ኢማን ስትወልድልህ ትቀምሰዋለህ!"
አልኩት።

ወዲያዉ የማዋለጃዉ ክፍል በር ሲከፈት አየን። ከተቀመጥንበት
ተነሳን። ከክፍሉ አንድ ዉሀ ሰማያዊ የህክምና ልብስ የለበሰች
ሴት ወጥታ እነመግፊራን ማናገር ጀመረች። ወደ ክፍሉ
በፍጥነት እየተራመድን ተጠጋን። የህፃን ልጅ ለቅሶ ይሰማል።

የነመግፊራ ፊት ላይ ደስታ ይነበባል። ወዲያዉ መሬት ላይ
በግንባሬ ተደፍቼ ጌታዬን አመሰገንኩ። እነመግፊን ተከትዬ ወደ
ማዋለጃ ክፍሉ ገባሁ። ሀዩዬ ፊቷ በላብ ተጠምቆ ተጋድማለች።

ስታየኝ ፈገግ አለች። ተንደርድሬ ሄጄ አልጋዉ አጠገብ ተንበርክኬ
እጇን ያዝኩት። ጠጋ ብዬ ግንባሯን ሳምኳት።
"ደሞ አሁን ቆንጆ የሴት ስም እንፈልግ!" አለች መግፊራ! ልጄ
ሴት ነበረች። ደስ አለኝ። ደስታዬ ወደር የለዉም። በጣም
ደስስስስ አለኝ።
"ያንተንም ጉድ እናየዋለን ሰዒዶ!" አለች ሀዩ ወደ ሰዒድ እያየች።
"እስኪ አላህ ያድርሰን!" አለ እየተሽኮረመመ።

ወዲያዉ ሀኪሞቹ ግርግሩን እንድንቀንስ እና እንድንወጣ አዘዙን።
እናቷ ብቻ ቀሩ። እኔና መግፊራ ለጊዜዉ የሚያስፈልጉ ነገሮችን
ለመግዛት ሄድን።
.
ይቀጥላል.....

ይቀላቀሉን

@eslamik_tube